በአሁኑ ሰዓት የኦክስጅን እጥረት በሆስፒታሎች ማጋጠሙን የህብረተሰብ ጤና ኢንስቲትዩት አስታወቀ


የኮቪድ 19 ወረርሽኝ ከእለት ወደ እለት በከፍተኛ ደረጃ ከመሰራጨቱም በላይ ሰብዓዊ ኢኮኖሚያዊ ማህበራዊ ችግሮችን እያስከተለ ይገኛል ተብሏል፡፡

ወደ ፅኑ ህሙማን ክፍል የሚገቡ ህሙማን ቁጥርም ከ 7 ሳምንታት በፊት 180 የነበረ ሲሆን በአሁኑ ሰዓት 602 ግለሰቦች በፅኑ ህሙማን ክፍል ውስጥ ክትትል እየተደረገላቸው እንደሚገኝና በዚህም በየሆስፒታሉ የኦክስጅን እጥረት እያጋጠመ መሆኑን ኢኒስቲትዩቱ አስታውቋል፡፡

በኮቪድ 19 ወረርሽኝ የመያዝ ምጣኔ ከ6 ሳምንታት በፊት 1.6 በመቶ የነበረ ሲሆን አሁን ላይ በያዝነው ሳምንት በአማካይ ወደ 16.5 ከመቶ ከፍ ማለቱ ተነግሯል፡፡

ከ7 ሳምንታት በፊት 11 ለሚሆኑ ህሙማን ሰው ሰራሽ አጋዥ የመተንፈሻ መሳሪያ የሚፈልጉ የነበረ ሲሆን በአሁን ሰዓት ግን ይህን ሰው ሰራሽ መሳሪያ የሚጠብቁ ህሙማን ቁጥር ወደ 80 አድጓል ተብሏል፡፡

በኮቪድ 19 ህይወታቸውን የሚያጡ ግለሰቦችም ከ6 ሳምንታት በፊት 11 ሆኖ የተመዘገበ ሲሆን በአሁኑ ሰዓት ላይ ወደ 88 ከፍ ማለቱ ተነግሯል፡፡

ከዚህ በፊት በኮቪድ 19 ምክንያት ተመዝግቦ የነበረው የሞት ቁጥርም ከ85 በመቶ በላይ የሚሆኑት 45 ዓመት እድሜ ገደማ የሚጠጉ ቢሆንም አሁን ባለው ወቅታዊ መረጃ ግን ከ15-24 በሚገኙ የእድሜ ክልል ውስጥ ወረርሽኙ ጉዳት እያስከተለ እንደሚገኝ ተነግሯል፡፡

ውድ አድማጮቻችን እና ተከታዮቻችን የኢትዮ ኤፍ ኤም ስርጭቶችን ቻናላችንን እና ሌሎች ዝግጅቶችን ለመከታተል የቴሌግራም ቻናላችንን https://t.me/ethiofm107dot8 ይቀላቀሉ።

ሄኖክ ወ/ገብርኤል
ነሐሴ 25 ቀን 2013 ዓ.ም

FacebooktwitterredditpinterestlinkedinmailFacebooktwitterredditpinterestlinkedinmail

Leave a Reply

Your email address will not be published.