በጋምቤላ በደረሰ ግጭት የሶስት ሰዎች ህይወት ማለፉ ተነገረ፡፡

በጋምቤላ ከተማ ትናንት ማምሻውን በተፈጠረ ግጭት የሶስት ሰዎች ህይወት ሲያልፍ አምስት ሰዎች ላይ ከባድ ጉዳት መድረሱን የክልሉ ሠላምና ፀጥታ ጉዳይ ቢሮ ለኢትዮ ኤፍ ኤም አስታወቀ፡፡

የክልሉ ሰላምና ፀጥታ ጉዳዮች ቢሮ ኃላፊ አቶ ቶማስ ቱት ለክልሉ ፕሬስ ሴክሬታሪያት ጽህፈት ቤት እንደገለፁት በትላንትናው ዕለት ከጋምቤላ ከተማ 4 ኪሎ ሜትር ርቀት ላይ ከቀኑ 11 ሰዓት ከ30 አካባቢ ማንነታቸው ያልታወቁ አምስት ግለሰቦች በከፈቱት ተኩስ የአንድ ሰው ህይወት ሲያልፍ ሁለት ሰው ላይ ከባድ ጉዳት ደርሷል ብለዋል፡፡

ጉዳቱን ተከትሎ በከተማው በተከሰተው ግጭት የሁለት ሰዎች ህይወት ማለፉንና ሶስት ሰዎች ላይ ከፍተኛ ጉዳት መድረሱን ቢሮው አመላክቷል፡፡

በግጭቱ በአጠቃላይ የሶስት ሰዎች ህይወት ሲያልፍ አምስት ሰዎች ላይ ደግሞ ከባድ ጉዳት መድረሱን ያመለከተው ፀጥታ ቢሮው ጥፋተኞቹን ወደ ህግ ለማቅረብ የፀጥታ አካላት ያላሰለሰ ጥረት እያደረጉ እንደሚገኝ ተናግረዋል፡፡

ከግጭቱ ጋር ግንኙነት አላቸው የተባሉ አስር የሚደርሱ ግለሰቦች ቀደም ብሎ በህግ ቁጥጥር ስር ውለው ተገቢውን ማጣራት እየተከናወነ እንደሚገኝ ቢሮው አስታውቋል፡፡

ግጭቱ በተፈጠረበት በጋምቤላ ከተማ ያለው ሰላም ወደ ነበረበት እየተመለሰ መሆኑን የተገለፀ ሲሆን ህብረተሰቡ አካባቢውን ነቅቶ በመጠበቅ ከፀጥታ አካላት ጎን በመሆን አስፈላጊውን መረጃ እንዲሰጥም በቢሮው ሃላፊ ተጠይቋል፡፡

ውድ አድማጮቻችን እና ተከታዮቻችን የኢትዮ ኤፍ ኤም ስርጭቶችን ቻናላችንን እና ሌሎች ዝግጅቶችን ለመከታተል የቴሌግራም ቻናላችንን https://t.me/ethiofm107dot8 ይቀላቀሉ።

በየዉልሰዉ ገዝሙ
ነሐሴ 25 ቀን 2013 ዓ.ም

FacebooktwitterredditpinterestlinkedinmailFacebooktwitterredditpinterestlinkedinmail

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *