የኩላሊት ህሙማን እጥበት ለማድረግ በግል ሆስፒታል እስከ 36 ሺህ ብር ይጠይቃሉ ተባለ

የኩላሊት ህሙማን እጥበት ለማድረግ በግል ሆስፒታል ለአንድ ጊዜ እጥበት 3ሺህ በወር ደግሞ እስከ 36 ሺህ ብር ይጠይቃሉ ተብሏል።

ይሄንን ወጪ ለመቀነስ ለኩላሊት ህሙማን እጥበት ማድረጊያ በጤና ሚኒስቴር በግዢ ለመጀመርያ ዙር ይገባሉ የተባሉት 100 ማሽኖች እስካሁን ተገዝተው አልገቡም ሲሉ የኩላሊት ህመምተኞች እጥበት በጎ አድራጎት ድርጅት ስራ አስኪያጅ የሆኑት አቶ ሰለሞን አሰፋ ተናግረዋል።

በግዢ ይገባሉ የተባሉት ለኩላሊት ህሙማን እጥበት ማከናወኛ ማሽን ገብተው ቢሆን ኖሮ ለ አንድ እጥበት 500 ብር ብቻ ያስወጣል ብለዋል ።

በዚህም በቀን 400 የሚጠጉ ሰዎች አገልግሎት መስጠት ይችላል ተብሏል።

አሁን ባለው ሁኔታ ግን በግል ሆስፒታል ለአንድ እጥበት እስከ 3000 ብር እየተጠየቁ መሆኑን ስራ አስኪያጁ ተናግረዋል።

በረድኤት ገበየሁ
ነሃሴ 25 ቀን 2013 ዓ.ም

FacebooktwitterredditpinterestlinkedinmailFacebooktwitterredditpinterestlinkedinmail

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *