የአማራ ክልል ፕሬዝዳንት ዶክተር ይልቃል ከፋለ ካቀረቧቸው እጩዎች መካከል አቶ ጣሂር ሙሃመድ ይገኙበታል።

Posted Leave a commentPosted in የሀገር ውስጥ ዜና

አቶ ጣሂር ከአማራ ብሄራዊ ንቅናቄ (አብን) አመራሮች መካከል ሲሆኑ በአማራ ክልል የቱሪዝም ቢሮን በኃላፊነት እንዲመሩ ነው የቀረቡት። ኢትዮ ኤፍ ኤም 107.8 የኢትዮጵያውያንመስከረም 20 ቀን 2014 ዓ.ም

ዶ/ር ይልቃል ከፋለ አስረስ አማራ ክልል ርዕሰ መስተዳድር ሆነው ተመረጡ

Posted Leave a commentPosted in የሀገር ውስጥ ዜና

የአማራ ክልል ምክር ቤት ዶ/ር ይልቃል ከፋለ አስረስ የክልሉ ርዕሠ-መስተዳድር አድርጎ መርጧል፡፡ ዶ/ር ይልቃል ከፋለ በተለያዩ ትምህርት ኮሌጆች በመምህርነት፣ ዲን በመሆንና በደብረማርቆስ ዩኒቨርሲቲ ም/ፕሬዝዳንትና ፕሬዝዳንት በመሆን ውጤታማ ሀላፊነትን የተወጡ አመራር መሆናቸው ተገልጿል፡፡ ኢትዮ ኤፍ ኤም 107.8 የኢትዮጵያውያንመስከረም 20 ቀን 2014 ዓ.ም

ራሱን የስብከት እና የትግል ንቅናቄ ብሎ የሚጠራው አዲስ ጅሃዳዊ ቡድን የሱዳን ሰላዮችን መግደሉ ተነግሯል

Posted Leave a commentPosted in የውጭ ዜና

እምብዛም እውቅና የሌለው ራሱን የጅሃዲስት ቡድን በሚል የሚጠራው አዲስ ሃይል ስድስት የሱዳን የስለላ መኮንኖችን መግደሉን በትላንትናው እለት አስታውቋል። እንደ ቢቢሲ አፍሪካ ዘገባ መንግስት ጥቃቱ ራሱን እስላማዊ መንግስት ብሎ ከሚጠራው (አይ ኤስ) ቡድን ታጣቂዎች ጋር እንደሚገናኝ ገልጻል ፡፡ ይህንን የመንግስት ወንጀላ ያጣጣለው ራሱን የስብከት እና የትግል ንቅናቄ ብሎ የሚጠራው ጅሃዲስት ቡድን ከአይ ኤስ ጋር ምንም አይነት […]

የልብ ቀዶ ጥገና ለማድረግ ከ7 ሺህ በላይ ህጻናት ወረፋ በመጠባበቅ ላይ እንደሆኑ ሰማን

Posted Leave a commentPosted in የሀገር ውስጥ ዜና

በኢትዮጵያ የልብ ቀዶ ህክምና ለማድረግ ከ7ሺህ በላይ ህጻናት ወረፋ በመጠባበቅ ላይ መሆናቸውን የሰማነው ከልብ ህሙማን ህጻናት መርጃ ማእከል ነው፡፡ የኢትዮጵያ የልብ ህሙማን ህጻናት መርጃ ማእከል ዋና ስራ አስፈጻሚ አቶ ህሩይ አሊ በየአመቱ እስከ 500 የሚደርሱ ህጻናት የልብ ቀዶ ህክምና እየተደረገላቸው እንደሚገኝ እና ቀዶ ህክምና የሚፈልጉ ህጻናት ቁጥር በየቀኑ እንደሚጨምር ኢትዮ ኤፍ ኤም ከሃላፊው ሰምቷል፡፡ ይህ […]

የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ምክር ቤት በአሁን ሰአት የከተማ አስተዳደሩን አስፈፃሚ አካላት መልሶ ለማደራጀት በተዘጋጀው 101 አንቀፆች ባሉት ረቂቅ አዋጅ ላይ እየተወያየ ነው፡፡

Posted Leave a commentPosted in የሀገር ውስጥ ዜና

በረቂቅ አዋጁ መሰረት ካለፈው ምክር ቤት 61 የነበሩት አጠቃላይ የአስፈፃሚ አካላት በአዲሱ ምክር ቤት 46 ሆኖ ሲቀርብ፣ የካቢኔ አባላት ደግሞ 24 እና በከንቲባ እንደ አስፈላጊነታቸው የሚሰየሙ ሌሎች ተቋማትን ጨምሮ አዳዲስ የካቢኔ አባላት የሆኑ ተቋማትን መያዙን ፋና ዘግቧል፡፡ በዚህም መሰረት የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር አስፈፃሚ አካላት መልሶ ለማደራጀት በተዘጋጀው ረቂቅ አዋጅ ላይ በካቢኔ ደረጃ የተደራጁ ተቋማት […]

በከተማችን የምናካሄዳቸው ሁሉም የልማት ስራዎች በሂደታቸውም ሆነ በውጤታቸው ተጨባጭ ለውጥ እንዲያመጡ ለማድረግ በትኩረት እንሰራን ሲሉ የአዲስ አበባ ከተማ ከንቲባ ወ/ሮ አዳነች አቤቤ ተናገሩ፡፡

Posted Leave a commentPosted in የሀገር ውስጥ ዜና

በዛሬው እለት እየተካሄደ በሚገኘው የአዲስ አበባ ከተማ ምክር ቤት ምስረታ ስነ ስርዓት ላይ ወ/ሮ አዳነች አቤቤ የከተማዋ ከንቲባ ሆነው ከተሾሙ በኋላ ባደረጉት ንግግር፤ በከተማዋ የምንሰራቸው ሁሉም ኢኮኖሚዊ እንቅስቃሴዎች በከታማችን ነዋሪዎች ላይ ተጨባጭ ለውጥን እንዲያመጡ እንሰራን ብለዋል፡፡ በከተማችን ላይ ምርትና አገልግሎት አቅርቦቶችን ለማሻሻል ሲባል በጥናት ለመለየት ይሰራል ያሉት ወ/ሮ አዳነች የከተማዋን የመልማት አቅም ለማጎልበት በትብብር እንሰራለን […]

የአዲስ አበባ ከተማ ምክር ቤትም ወይዘሮ አዳነች አቤቤን የከተማው ከንቲባ በማድረግ መርጧል፡፡

Posted Leave a commentPosted in የሀገር ውስጥ ዜና

ወ/ሮ አዳነች አቤቤ ከነሀሴ 12 ቀን 2012 ዓ.ም ጀምሮ የአዲስ አበባ ምክትል ከንቲባ በመሆን ያገለገሉ ሲሆን አሁንም በድጋሚ ከተማዋን በከንቲባነት እንዲመሩ ተመርጠዋል፡፡ ወ/ሮ አዳነች ከተማዋን ከ 12 ወራት በላይ በምክትል ከንቲባ ማእረግ እየመሩ የሚገኙ ሲሆን ፣ ምክር ቤት በዛሬው እለት ባካሄደው ጉባዔም ከንቲባ አድርጎ ወይዘሮ አዳነች አቤቤ በከንቲባነት ሾሟል፡፡ ወይዘሮ አዳነች አቤቤ የአዳማ ከተማ ከንቲባ፤ […]

ወ/ሮ ፋይዛ መሃመድ የአዲስ አበባ ከተማ ምክር ቤት አባላት ምክትል አፈ ጉባኤ እንዲሆኑ በሙሉ ድምጽ ተሾሙ

Posted Leave a commentPosted in የሀገር ውስጥ ዜና

አዲስ አበባ ከተማ አዲስ ምክር ቤት ምስረታ ስነ-ስርአት እየተካሄደ ነው። በማዘጋጃ ቤት ቴአትር እና ባህል አዳራሽ እየተካሄደ ባለው አዲስ ምክር ቤት ምስረታ ስነ-ስርአት በቀጣይ አምስት ዓመታት ምክር ቤቱን በአፈጉባኤነት እና በምክትል አፈጉባኤ እንዲሁም የከንቲባ ሹመት እና የካቢኔ አባላት ሹመት በቅደም ተከተል ለማካሄድ ባቀደው መሰረት በእጩነት አቅርቧቸው የነበሩት ወ/ሮ ፋይዛ ሞሃመድ 138 ድጋፍ አግኝተው ተሹመዋል፡፡ ወ/ሮ […]

ወ/ሮ ቡዜና አልቃድር የአዲስ አበባ ምክር ቤት አፈጉባኤ በመሆን ተመርጠዋል።

Posted Leave a commentPosted in የሀገር ውስጥ ዜና

በዛሬው እለት በአዲስ አበባ ምክር ቤት መሰብሰቢያ አዳራሽ እየተካሄደ ባለው የከተማው ምክር ቤት ምስረታ ወ/ሮ ቡዜና አልቃድር በ 138 ድምጽ በማግኘት ተመርጠዋል። ወ/ሮ ቡዜና ከዚህ ቀደም በተለያዩ የስራ ዘርፎች ላይ በሃላፊነት ያገለገሉ ሲሆን በአሁኑ ሰኣት የባህልና ቱሪዝም ሚኒስቴር ሚኒስትር ዴኤታ ሆነው እያገለገሉ ይገኛሉ። በመቅደላዊት ደረጄመስከረም 18 ቀን 2014 ዓ.ም

የመስቀል በአልን ምክንያት በማድረግ ከታሪፍ በላይ በጠየቁ 50 አሽከርካሪዎች ላይ ህጋዊ እርምጃ መወሰዱን የፌደራል ትራንስፖርት ባለስልጣን ገለጸ፡፡

Posted Leave a commentPosted in የሀገር ውስጥ ዜና

የፌደራል ትራንስፖርት ባለስልጣን ከመስቀል በአል አከባበር ጋር በተያያዘ ያልተገባ የዋጋ ጭማሪ በሚያደርጉ አሽከርካሪዎች ላይ ህጋዊ እርምጃ እየወሰድኩ እገኛለሁ ሲል አስታውቋል፡፡ በፌደራል ትራንስፖርት ባለስልጣን የመለስተኛ እና አነስተኛ መናሃሪያ የአዲስ ክፍለ ከተማ መናሃሪያ የቡድን መሪ አቶ ውብሸት ደመላሽ ለኢትዮ ኤፍ ኤም እንደተናገሩት የመስቀልን በዓል ለማክበር ከመዲናዋ ውደ ተለያዩ የአገሪቱ ክፍሎች በሚንቀሳቀሱ ተጓዞች ላይ የሚደረግን የታሪፍ ጭማሪ ለመቆጣጠር […]