ቮዳፎን ወደ ኢትዮጵያ እንዲገባ ከአዉሮፓ ኮሚሽን ፈቃድ አገኘ፡፡

ኮሚሽኑ ቮዳፎን ከሳፋሪ ኮም ጋር በሚኖረዉ ሽርክና ያልተገባ የንግድ ዉድድር ሊፈጠር ይችላል በሚል ምርመራ ሲያደረግ መቆየቱን የኢስት አፍሪካን ሪፖርት ያሳያል፡፡

ይሁንና ኮሚሽኑ ያደረገዉ የምርመራ ዉጤት ጥምረቱ ፍትሃዊ ዉድድር ለማድረግ ምንም የሚገድብ ነገር እንደሌለ አመላክቷል፡፡

በዚህም ቮዳፎን ሳፋሪ ኮም በሚመራዉና የእንግሊዝ የልማትና ፋይናንስ ኤጀንሲ ሲዲሲ ግሩፕ እና የጃፓኑ ሱሚቶሞ ኮርፖሬሽን በሚገኙበት ጥምረት እንዲቀላቀል ፈቃድ ማግኘቱ ታዉቋል፡፡

ከአዉሮፓ ህብረት ጋር የሚሰሩ ድርጅቶች ጥምረት በሚፈጥሩበት ወቅት በመካከላቸዉ ምንም አይነት ያልተገባ የንግድ ዉድድር እንዳይፈጠር ጥንቃቄ ማድረግ እንዳለባቸዉ ህብረቱ እንደሚያዝዝ ሪፖርቱ ያመላክታል፡፡

“የግሎባል ፓርትነርሽፕ ፎር ኢትዮጵያ” ድርጅት አንዱ የሆነው የጃፓኑ ሱሚቶሞ፣ በቴሌኮም ዘርፍ የውጭ ባለሀብቶች እንዲሳተፉ መንግሥት ባሳለፈው ውሳኔ መሠረት ጨረታውን ማሸነፉ የሚታወቅ ሲሆን

በቀጣይ አምስት ዓመታት ውስጥ በኢትዮጵያ በቴሌኮም ዘርፍ ከሁለት ቢሊዮን የአሜሪካ ዶላር በላይ ኢንቨስት ለማድረግ ፍላጎት እንዳለው መግለጹ ይታወሳል፡፡

ምንጭ፡- Mobaile Europe.com

በሙሉቀን አሰፋ
ጳጉሜ 04 ቀን 2013 ዓ.ም

FacebooktwitterredditpinterestlinkedinmailFacebooktwitterredditpinterestlinkedinmail

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *