በትግራይ ፤ በኤርትራ ስደተኞች ላይ የጦር ወንጀል እየተፈፀመ እንደሆነ የአለም አቀፍ ሰብአዊ መብት ተሟጋቹ ሂዩማን ራይትስዎች ገለፀ

የኤርትራ ስደተኞች ትግራይ ውስጥ ባለው ሀይል ታፍነው ይታሰራሉ፣ ይደፈራሉ፣ ይገደላሉ ብሏል ሂዩማን ራይትስ ዎች፡፡

እንደ አለም አቀፉ የሰብአዊ መብት ተሟጋች ሂዩማን ራይትስ ዎች ሪፖርት በኤርትራ ስደተኞች ላይ የሚፈፀሙት እነዚህ የሰብአዊ መብት ጥሰቶች በህወሀት ብቻ ሳይሆን ከኢትዮጵያ ፌደራል ሀይል ጎን ቆመው በሚዋጉት የኤርትራ ሀይሎች ጭምር እንደሆነም አንስቷል፡

በሺዎች የሚቀጠሩ ኤርትራውያን ስደተኞች በትግራይ ካምፕ ተጠልለው ይገኛሉ፡፡

የሰብአዊ መብት ተሟጋቹ የአፍረካ ቀንድ ዳይሬክተር እንደተናገሩት ፤ በትግራይ ዘግናኝ ግድያዎች፣ አስገድዶ መድፈሮች እና ዘረፋዎች በኤርትራ ስደተኞች ላይ እየተፈፀሙ ነው፡፡

እነዚህ ሁሉ ግልፅ የጦርነት ወንጀሎች ናቸው ሲሉ ተናግረዋል፡፡

ኤርትራ ለዚህ ክስ እስካሁን ምንም አላለችም፤ ከዚህ ቀደም ግን ክሱን ውድቅ አድርጋ ነበር፡፡

ቢቢሲ ሮይተርስ የዜና ወኪልን ጠቅሶ እንደዘገበው ከፍተኛ ቁጥር ያለው የኤርትራ ጦር በትግራይ ይገኛል፡፡

ሔኖክ አስራት
መስከረም 06 ቀን 2014 ዓ.ም

FacebooktwitterredditpinterestlinkedinmailFacebooktwitterredditpinterestlinkedinmail

Leave a Reply

Your email address will not be published.