በዘንድሮው አመት ከ17ሚሊዮን በላይ የሚሆኑ ህፃናት ተጠቃሚ የሚያደርግ የፖሊዮ ክትባት ዘመቻ በኢፌዴሪ የጤና ጥበቃ ሚንስቴር ዴኤታ ዶ/ር ደረጀ ዱጉማ በተገኙበት በይፋ ተጀመረ

Posted Leave a commentPosted in የሀገር ውስጥ ዜና

ሃገር አቀፍ የፖሊዮ ክትባት ዘመቻ በጌዴኦ ዞን በዲላ ከተማ በኢፌዴሪ የጤና ጥበቃ ሚንስቴር ዴኤታ ዶ/ር ደረጀ ዱጉማ በተገኙበት በይፋ ተጀምሯል ። በመረሃ ግብሩ በመገኘት ንግግር ያደረጉት የኢፌዴሪ የጤና ጥበቃ ማኒስቴር ዴኤታ ደረጃ ዱጉማ ዶ/ር በወቅቱ እንደተናገሩት የህብረተሰቡን የጤና ስርዓት ለመጠበቅ በትኩረት ይሰራል ብለዋል ። በሀገር አቀፍ ደረጃ ከጥቅምት 12 እስከ 15/2014 ዓ.ም ድረስ በሚቆየው በቤት […]

የተከፈተብንን ጥቃት ለመመከት መፍትሄው የተደራጀ ንቅናቄ ነው ሲል የመንግሥት ኮሙዩኒኬሽን አገልግሎት አስታወቀ፡፡

Posted Leave a commentPosted in የሀገር ውስጥ ዜና

የመንግሥት ኮሙዩኒኬሽን አገልግሎት በወቅታዊ ጉዳይ ላይ መግለጫ የሰጠ ሲሆን፤ ካለፈው ሳምንት ጀምሮ አሸባሪው የሕወሓት ቡድን አለኝ የሚለውን ኃይል በማሰባሰብ በአፋርና በአማራ ክልሎች ባሉት ግንባሮች መጠነ ሰፊ ጥቃት መሰንዘሩ ይታወቃል ብሏል። በዚህ ጥቃትም በርካታ ንጹሃን ዜጎችን ገድሏል፤ ንብረት ዘርፏል፤ የአንድ ቤተሰብ አባላትን ጋዝ አርከፍክፎ አቃጥሏል፤ በእነዚህ አካባቢዎች ሁሉም ማኅበራዊና ምጣኔሃብታዊ እንቅስቃሴዎች እንዲገቱ አድርጓል ሲልም አክሏል። ቡድኑ […]

የሞባይል ፍቅር ከጆሮ እስከ ሆድ በግብጽ

Posted Leave a commentPosted in የውጭ ዜና

በሰው ሆድ ውስጥ ሞባይል ተገኘ ብትባሉ ምን ትላላችሁ? ከዚህ በፊት በኢትዮጵያ በአርባምንጭ ከተማ በአንድ ግለሰብ ሆድ ውስጥ የተለያዩ ሚስማሮችን ጨምሮ የተለያዩ ስለታማ ነገሮች እንደተገኙ ነግረናችሁ ነበር፡፡ አሁን ከወደ ግብጽ የተሰማው ወሬ በርካቶችን አስገርሟል በግብጽ በአንድ ግለሰብ ሆድ ውስጥ የሞባይል ቀፎ መገኘቱ ነው የተሰማው በግብጽ አስዋን ዩኒቨርስቲ ሆስፒታል ውስጥ በአንድ ግለሰብ ሆድ ውስጥ መጠኑ አነስተኛ የሆነ […]

የዶሮ እና እንስሳት ሃብት ዓዉደርዕይ በቀጣዩ ሳምንት በአዲስ አበባ ይካሄዳል፡፡

Posted Leave a commentPosted in የሀገር ውስጥ ዜና

10ኛው የኢትዮ ፓልተሪ ኤክስፖ እና 6ኛው የአፍሪካ እንስሳት አውደርእይና ጉባኤ ከጥቅምት በአካል ከጥቅምት 18-20 እንዲሁም ከጥቅምት 22- ህዳር 22 2014 ዓ.ም ደግሞ በበይነመረብ ይደረጋል ተብሏል፡፡ አዘጋጆቹ ፕራና ኤቨንትስ እና መቀመጫውን ሱዳን ያደረገው ኤክስፖ ቲም በዛሬዉ እለት እንዳስታወቁት፣ በአዉደርዕዩ ላይ ከተለያዩ ሃገራት የተዉጣጡ የዘርፉ አንቀሳቃሾች ይሳተፉበታል፡፡ አዉደርዕዩ ለዘርፉ አስፈላጊ የሆኑ ቴክኖሎጂዎች የሚቀርቡበት ከመሆኑም ባሻገር ያሉበትን ችግሮች […]

የምዕራባውያን ጫና ኢትዮጵያ ውስጥ ያለውን እውነታ ካለማወቅ ሳይሆን ሆን ተብሎ የተደረገ ስለመሆኑ የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር አስታወቀ

Posted Leave a commentPosted in የሀገር ውስጥ ዜና

የሚኒስቴሩ ቃል አቀባይ አምባሳደር ዲና ሙፋቲ እንዳስታወቁት በሰሜን ኢትዮጵያ እየተደረገ ባለው ጦርነት ምዕራባውያን በኢትዮጵያ መንግስት ላይ ጫና እያደረጉ ያሉት ከዲፕሎማሲ ድክመትና እውነታውን ካለማስረዳት የመነጨ ሳይሆን ጥቅማቸው ስለተነካባቸው ነው ብለዋል ። በተለይ ፅንፍ የያዙ የምዕራባዊያን መገናኛ ብዙኃን አሸባሪው ሕወሓት ኢሰብኣዊ ጥቃቶችን ሲያደርስ ዝምታ መምረጣቸውን በተቃራኒው ቡድኑ ተመታሁ ሲል አግዝፈው ማራገባቸው ያልተገባ ድርጊት መሆኑ ተነግሯቸዋል ተብሏል። አምባሳደር […]

በትግራይ እና ወልዲያ ዩኒቨርሲቲ ሲማሩ የነበሩ ተማሪዎች በሌሎች ዩኒቨርሲቲዎች እንዲመደቡ ተወሰነ፡፡

Posted Leave a commentPosted in የሀገር ውስጥ ዜና

በትግራይ ክልል ባሉ ዩኒቨርሲቲዎችና በወልድያ ዩኒቨርሲቲ ሲማሩ የነበሩ መደበኛ ተማሪዎች በጊዜያዊነት ወደ ሌሎች ዩኒቨርሲቲዎች እንዲመደቡ ትምህርት ሚኒስቴር ውሳኔ አስተላልፏል፡፡ በትግራይ ክልል በሚገኙ ዩኒቨርሲቲዎች እና ወልዲያ የኒቨርሲቲ ሲማሩ የነበሩ መደበኛ ተማሪዎች ወደ ሌሎች ዩኒቨርሲቲዎች በጊዜያዊነት ለመመደብ የመመዝገቢያ ገፅ ተከፍቶ ተማሪዎች እንደሚመዘገቡ እና ምደባ እንደሚካሄድም ተገልጿል፡፡ በዚህም በዩኒቨርስቲዎቹ ትምህርትቸውን ሲከታተሉ የነበሩ ተማሪዎች አስፈላጊውን የትምህርት ማስረጃቸውን በማዘጋጀት ከ […]

ለትምህርት ቤቶች የትራንስፖርት አገልግሎት የሚሰጡ ባለ ታክሲዎች ከድርጊታቸው እንዲቆጠቡ ተጠየቀ፡፡

Posted Leave a commentPosted in የሀገር ውስጥ ዜና

ለህዝብ ትራንስፖርት መስጠት ሲገባቸው በየትምህርት ቤቶች ተማሪዎችን የሚያመላልሱ ታክሲዎች ህጋዊ እርምጃ ሳይጣልባቸው ለህዝቡ አገልግሎት እንዲሰጡ ተጠይቀዋል፡፡ የትራንስፖርት ቢሮ ከሰጣቸው ፍቃድ ውጪ ለተማሪዎች ሰርቪስ የሚሰጡ ባለታክሲዎች በትራንስፖርት አቅርቦቱ ላይ ችግር መፍጠራቸው ነው የአዲስ አበባ ትራንስፖርት ቢሮ ለኢትዩ ኤፍ ኤም ተናግሯል፡፡ የአዲስ አበባ ትራንስፖርት ቢሮ በየትምህርት ቤቶቹ ለተማሪዎች ሰርቪስ እየሰጡ የሚገኙ ታክሲዎች ከዛሬ ጀምሮ እየሰጡ ያሉትን አገልግሎት […]

ጠቅላይ ሚኒስትር ዶ/ር ዐቢይ አህመድ ዶ/ር ለከፍተኛ የመንግስት ሃላፊነት ቦታዎች ሹመቶች ሰጡ:-

Posted Leave a commentPosted in የሀገር ውስጥ ዜና

ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አህመድ ለ22ቱ ሚኒስቴር መስሪያ ቤቶች እና ለጠቅላይ ሚኒስትር ጽ/ቤት ሚኒስትር ዴኤታዎችን እንዲሁም ለሌሎች ሁለት ተቋማት ኮሚሽነሮችን ሾመዋል፡፡ ከተሿሚዎቹ መካከል የተፎካካሪ ፓርቲ አመራር አካላት የተካተቱ ሲሆን ከእናት ፓርቲ ወ/ሮ ጥሩማር አባተ የፕላንና ልማት ሚኒስቴር ሚኒስትር ዴኤታ እንዲሁም ከነጻነትና እኩልነት ፓርቲ ወ/ሮ ነብያ መሃመድ የስራና ክህሎት ሚኒስቴር ሚኒስትር ዴኤታ ሆነው ተሹመዋል፡፡ የመስሪያ ቤቱ ስም፣የተሿሚው […]

ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አህመድ (ዶ/ር) ለከፍተኛ የመንግስት ሃላፊነት ቦታዎች ሹመቶች ሠጡ::

Posted Leave a commentPosted in የሀገር ውስጥ ዜና

ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አህመድ (ዶ/ር) በዛሬው እለት አቶ ተፈሪ ፍቅሬን የጠቅላይ ሚኒስትር ጽ/ቤት ሃላፊ እና የካቢኔ ጉዳዮች ሚኒስትር አድርገው በድጋሚ የሾሙ ሲሆን ለ4 ከፍተኛ የሃላፊነት መደቦችም በሚኒስቴር ማእረግ የሚከተሉትን ሹመቶች ሰጥተዋል፡- አቶ አደም ፋራህ – በሚኒስትር ማዕረግ የዲሞክራሲ ስርዓት ግንባታ ማስተባበሪያ ማዕከል ዋና አስተባባሪ አቶ ተስፋዬ ቤልጅጌ – በሚኒስትር ማዕረግ በሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት የመንግስት […]

ቻይናዊያን ተማሪዎች ለረጅም ሰዓት የምትበር ድሮን በመስራት ክብረ ወሰን ሰበሩ::

Posted Leave a commentPosted in የውጭ ዜና

በቻይናዊያን የዩኒቨርሲቲ ተማሪዎች የተሰራች መሳርያ አልባ ድሮን ያለ እረፍት ለረጅም ሰዓት የበረረች ድሮን በመባል የዓለም ክብረ ወሰንን ሰብራለች፡፡ ፌንግ አርዩ 3-100 የተሰኘችው ይህች በቤጂንግ የኤሮናቲክስ እና አስትሮናቲክስ ዩኒቨርሲቲ ተማሪዎች የተሰራች ድሮን ያለ ማቋረጥ ለ80 ሰዓት ከ46 ደቂቃ ከ35 ሴኮንድ በመብረር ነው ቀድሞ በቦይንግ ስር በሚተዳደረው ኦሪዮን በተሰኘ ተቋም በ80 ሰዓት፣ ከ2 ደቂቃ ከ52 ሴኮንድ ተይዞ […]