“ያደረግሁት አስተዋጽኦ በፈታኞቹ ወቅቶችና ሰአታት ሀገሬን ቀና አድርጓታል ብዬ አምናለሁ፣በቀጣይ ገሬ በምትፈልገኝ አገልግሎት የምሰማራ ይሆናል”- ዶ/ር ኢ/ር ስለሺ በቀለ” ብለዋል


በኢትዮጵያ መንግስት አዲሱ ካቢኔ ውስጥ ያልተካተቱት የቀድሞው የውኃ መስኖና ኢነርጅ ሚኒስትር ዶ/ር ኢንጂነር ስለሺ በቀለ አለመካተታቸው በርካቶችን እያነጋገረ ነው።

ይህንን አስመልክቶም ስለሺ በቀለ (ዶ/ር ኢ/ር ) በይፋዊ የፌስቡክ ገጻቸው መልዕክት አስተላልፈዋል።

በዚህም መሰረት “በቀጣይ አገሬ በምትፈልገኝ አገልግሎት የምሰማራ ይሆናል” ሲሉ የቀድሞው ሚኒስትር ተናግረዋል።

የመስኖ እና ቆላማ አካባቢዎች ልማት ሚኒስትር በመሆን ለተሾሙት ኢንጂነር አይሻ መሀመድ እና የውሃና ኢነርጂ ሚኒስትር ሆነው ለተሾሙት ዶ/ር ኢ/ር ሃብታሙ ኢተፋም መልካም ምኞት አስተላልፈዋል።

ላለፉት አምሰት አመታት ሚኒስትር በመሆን በቅንነት፤ በታማኝነትና በሚችሉት ሁሉ ሀገራቸውን ማገልገላቸውንም ሚኒስትሩ ጠቅሰዋል።

ዶ/ር ኢ/ር ስለሺ “ብዙ አስቸጋሪ ጊዜያትንም አሳልፈናል፤ ግድባችንም በጥቂት ወራት ሀይል ያመነጫል፤ በዚህና በሌሎችም መስኮች ያደረግሁት አስተዋጽኦ በፈታኞቹ ወቅቶችና ሰአታት ሀገሬን ቀና አድርጓታል ብዬ አምናለሁ“ ሲሉም ነው መልዕክት ያስተላለፉት፡፡

በቀጣይ ኢትዮጵያ በምትፈልጋቸው አገልግሎት እንደሚሰማሩም አል-ዐይን ዘግቧል፡፡

ኢትዮ ኤፍ ኤም 107.8 የኢትዮጵያውያን
መስከረም 26 ቀን 2014 ዓ.ም

FacebooktwitterredditpinterestlinkedinmailFacebooktwitterredditpinterestlinkedinmail

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *