ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አህመድ (ዶ/ር) በዛሬው እለት አቶ ተፈሪ ፍቅሬን የጠቅላይ ሚኒስትር ጽ/ቤት ሃላፊ እና የካቢኔ ጉዳዮች ሚኒስትር አድርገው በድጋሚ የሾሙ ሲሆን ለ4 ከፍተኛ የሃላፊነት መደቦችም በሚኒስቴር ማእረግ የሚከተሉትን ሹመቶች ሰጥተዋል፡-
- አቶ አደም ፋራህ – በሚኒስትር ማዕረግ የዲሞክራሲ ስርዓት ግንባታ ማስተባበሪያ ማዕከል ዋና አስተባባሪ
- አቶ ተስፋዬ ቤልጅጌ – በሚኒስትር ማዕረግ በሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት የመንግስት ተጠሪ
- ዶ/ር ስለሺ በቀለ – በሚኒስትር ማዕረግ የድንበር ተሻጋሪ ወንዞችና የህዳሴግድብ ዋና ተደራዳሪና አማካሪ
- ዶ/ር ለገሰ ቱሉ – በሚኒስትር ማዕረግ የመንግስት ኮሙኒኬሽን አገልግሎት ኃላፊ
በተጨማሪም፡
- ዶ/ር ምህረት ደበበ – የአፍሪካ አመራር ልህቀት አካዳሚ ፕሬዚዳንት፤
- አቶ ፍሰሃ ይታገሱ – የኢትዮጵያ ብሮድካስት ኮርፖሬሽን ዋና ሥራ አስፈፃሚ፤
- እንዲሁም አቶ አብዱራህማን ሩቤ – የኢትዮጵያ ብሮድካስት ኮርፖሬሽን ምክትል ዋና ሥራ አስፈፃሚ ሆነው ተሹመዋል፡፡
ኢትዮ ኤፍ ኤም 107.8 የኢትዮጵያውያን
መስከረም 27 ቀን 2014 ዓ.ም











