ለትምህርት ቤቶች የትራንስፖርት አገልግሎት የሚሰጡ ባለ ታክሲዎች ከድርጊታቸው እንዲቆጠቡ ተጠየቀ፡፡

ለህዝብ ትራንስፖርት መስጠት ሲገባቸው በየትምህርት ቤቶች ተማሪዎችን የሚያመላልሱ ታክሲዎች ህጋዊ እርምጃ ሳይጣልባቸው ለህዝቡ አገልግሎት እንዲሰጡ ተጠይቀዋል፡፡

የትራንስፖርት ቢሮ ከሰጣቸው ፍቃድ ውጪ ለተማሪዎች ሰርቪስ የሚሰጡ ባለታክሲዎች በትራንስፖርት አቅርቦቱ ላይ ችግር መፍጠራቸው ነው የአዲስ አበባ ትራንስፖርት ቢሮ ለኢትዩ ኤፍ ኤም ተናግሯል፡፡

የአዲስ አበባ ትራንስፖርት ቢሮ በየትምህርት ቤቶቹ ለተማሪዎች ሰርቪስ እየሰጡ የሚገኙ ታክሲዎች ከዛሬ ጀምሮ እየሰጡ ያሉትን አገልግሎት እንዲያቆሙ ሲል አሳስቧል፡፡

መንግስት በትምህርት ቤቶች የትራንስፖርት ችግር እንዳይጉላሉ በማሰብ 100 ያህል የተማሪ ሰርቪስ ተሽከርካሪዎችን አሰማርቶ እንደሚገኝም ነው ቢሮው ያስታወቀው፡፡

የአዲስ አበባ ትራንስፖርት ቢሮ የኮሚኒኬሽን ዳሬክተር አቶ አረጋዊ ማሩ ለኢትዮ ኤፍ ኤም እንደተናገሩት ባለ ታክሲዎች አገልግሎት መስጠት ያለባቸው ለትምህርት ቤቶች ሳይሆን ለህዝቡ ነው ብለዋል፡፡

ፍቃድ የተሰጣቸው ህዝቡን ለማገልገል እንጂ በየትምህርት ቤቱ ለተማሪዎች ሰርቪስ እንዲሰጡ አይደለም ሲሉም ተናግረዋል፡፡

ትምህርት ቤቶች አካባቢ የትራንስፖርት እጥረት ካለም መንግስት እጥረቱን ይቀርፋል ብለዋል ዳሬክተሩ፡፡

በመሆኑም ለተማሪዎች ሰርቪስ እየሰጡ ያሉት ባለ ታክሲዎች ወደ ህጋዊ አሰራር እንዲገቡ ሲሉ ጥሪያቸውን አስተላልፈዋል፡፡

በአዲስ አበባ በህዝብ የትራንስፖርት አገልግሎት የተሰማሩ ወደ 11ሺህ የሚጠጉ ታክሲዎች እንዳሉ የተናገሩት አቶ አረጋዊ ማሩ ካለው ፍላጎት አንጻር እጅግ ዝቅተኛ ነው ብለዋል፡፡

አሁን ላይ በመዲናዋ ከ3.5 ሚሊየን ሰው በላይ የትራንስፖርት አገልግሎት እንደሚጠቀም ነው መረጃዎች የሚያሳዩት፡፡

ሔኖክ ወ/ገብርኤል
ጥቅምት 03 ቀን 2014 ዓ.ም

FacebooktwitterredditpinterestlinkedinmailFacebooktwitterredditpinterestlinkedinmail

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *