የምዕራባውያን ጫና ኢትዮጵያ ውስጥ ያለውን እውነታ ካለማወቅ ሳይሆን ሆን ተብሎ የተደረገ ስለመሆኑ የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር አስታወቀ


የሚኒስቴሩ ቃል አቀባይ አምባሳደር ዲና ሙፋቲ እንዳስታወቁት በሰሜን ኢትዮጵያ እየተደረገ ባለው ጦርነት ምዕራባውያን በኢትዮጵያ መንግስት ላይ ጫና እያደረጉ ያሉት ከዲፕሎማሲ ድክመትና እውነታውን ካለማስረዳት የመነጨ ሳይሆን ጥቅማቸው ስለተነካባቸው ነው ብለዋል ።

በተለይ ፅንፍ የያዙ የምዕራባዊያን መገናኛ ብዙኃን አሸባሪው ሕወሓት ኢሰብኣዊ ጥቃቶችን ሲያደርስ ዝምታ መምረጣቸውን በተቃራኒው ቡድኑ ተመታሁ ሲል አግዝፈው ማራገባቸው ያልተገባ ድርጊት መሆኑ ተነግሯቸዋል ተብሏል።

አምባሳደር ዲና፤ በሰብአዊ ድጋፍ ሰበብ አገር ውስጥ ገብተው ለሽብር ቡድኑ መሳሪያና የመገናኛ ዘዴዎችን ሲያስተላልፉ ተገኝተው ከአገር የተባረሩ ሰዎችም መሳያ ናቸው ብለዋል፡፡

ቃል አቀባዩ ይህን ያሉት በዛሬው ዕለት በሰጡት ሳምንታዊ ጋዜጣዊ መግለጫ ላይ ነው። በሳምንታዊ መግለጫቸው ስለ ግብጽና ሱዳን የጋራ ወታደራዊ ስምምነት እንዲሁም ባላፈው ሳምንት ስለተደረው 39ኛውየአፍሪካ ህብረት የሚኒስትሮች ስብሰባም እና ሌሎች ጉዳዮችን አንስተዋል፡፡

የ2063 የአፍሪካ አጀንዳ ከግጭት ነፃ የሆነች አህጉር መፍጠር እንዲሁም ሁሉም የህብረቱ አባል አገራት ያለምንም ቪዛ እንዲንቀሳቀሱ በሚለው ጭብጥ ላይ ሚንስትሮቹ መምከራቸውን ተገልጿል።

በሌላ በኩል በጂቡቲ የሚገኙ ኢንቨስተሮች ከኢትዮጵያ ጋር በቁም እንሰሰት ግብይት ለመስራት ውይይት ማድረጋቸው ተነግሯል።

በጂቡቲ በቁም እንሰሰት ሀብት ልማት ላይ የተሰማሩ አፍሪካውያን ባለሀብቶች ወደ አዲስ አበባ መጥተው ከባለድርሻ አካላት መስራታቸውንም አምባሳደር ዲና ተናግረዋል። ይህም አገሪቱ ወደ ውጭ የምትልከውን የቁም እንስሳት ገበያ ለማሳደግ ያስችላል ተብሏል።

አባቱ መረቀ

ጥቅምት 11 ቀን 2014 ዓ.ም

FacebooktwitterredditpinterestlinkedinmailFacebooktwitterredditpinterestlinkedinmail

Leave a Reply

Your email address will not be published.