የሞባይል ፍቅር ከጆሮ እስከ ሆድ በግብጽ

በሰው ሆድ ውስጥ ሞባይል ተገኘ ብትባሉ ምን ትላላችሁ?

ከዚህ በፊት በኢትዮጵያ በአርባምንጭ ከተማ በአንድ ግለሰብ ሆድ ውስጥ የተለያዩ ሚስማሮችን ጨምሮ የተለያዩ ስለታማ ነገሮች እንደተገኙ ነግረናችሁ ነበር፡፡

አሁን ከወደ ግብጽ የተሰማው ወሬ በርካቶችን አስገርሟል በግብጽ በአንድ ግለሰብ ሆድ ውስጥ የሞባይል ቀፎ መገኘቱ ነው የተሰማው በግብጽ አስዋን ዩኒቨርስቲ ሆስፒታል ውስጥ በአንድ ግለሰብ ሆድ ውስጥ መጠኑ አነስተኛ የሆነ ሞባይል ቀፎ መገኝቱ በርካቶችን አስደንቋል፡፡

ሞሀመድ እስማኤል ሞሀመድ የተባለው ግብጻዊ በአንድ ወቅት ውጦት የነበረው ይህ ሞባይል በቀዶ ጥገና ሊወጣለት መቻሉን ነው ኢዲቲ ሴንትራል ያስነበበው፡፡

ግለሰቡ ከፍተኛ የሆድ ህመም አጋጥሞት ወደ ሆስፒታል በሄደበት ቅጽበት ዶክተሮች ባደረጉለት ህክምና ነው የሞባይል ቀፎውን ሊያወጡለት የቻሉት፡፡

ዶክተሮች በቀዶ ጥገና ሞባይሉን ከማውጣታቸው በፊት በሲቲ ስካን አማካኘነት የተገኘውን ግኝት ለፖሊስ ማሳየታቸው ተከትሎ ነው ሞባይሉ ሊወጣለት የቻለው፡፡

ግለሰቡ ከስድስት ወራቶች በፊት ነበር ሞባይሉን ውጦት እንደነበረ ለፖሊሶች ያስረዳው ሲሆን ፣ ምንም አይነት የጤና ችግር የሌለበትና ስራውን በአግባቡ የሚሰራ እንደሆነም ነው ዶክተሮች የተናገሩት፡፡

ነገር ግን ላለፉት ሶስት ወራት በከባድ የሆድ ህመም ሲሰቃይ የቆየ ሲሆን ሞባይሉ ከወጣለት በኃላ ግን በመልካም ጤንነት ላይ ይገኛል ተብሏል ግለሰቡ አሁን ላይ ወደ ቀድሞ ጤንነቱ ተመልሶ መመገብ መጀመሩን ኦዲቲ ሴንትራል ያስነበበው፡፡

በሀገሪቱ ከሰባት አመታት በፊት አንድ ግለሰብ በእንቅልፍ ልቡ የጥረስ ቡሩሽ ውጦ እንደነበረ እና በቀዶ ጥገና አማካኝነት ሊወጣለት እንደተቻለም ነው ዶክተሮች የተናገሩት፡፡

ሔኖክ ወ/ገብርኤል
ጥቅምት 11 ቀን 2014

FacebooktwitterredditpinterestlinkedinmailFacebooktwitterredditpinterestlinkedinmail

Leave a Reply

Your email address will not be published.