የዶሮ እና እንስሳት ሃብት ዓዉደርዕይ በቀጣዩ ሳምንት በአዲስ አበባ ይካሄዳል፡፡

10ኛው የኢትዮ ፓልተሪ ኤክስፖ እና 6ኛው የአፍሪካ እንስሳት አውደርእይና ጉባኤ ከጥቅምት በአካል ከጥቅምት 18-20 እንዲሁም ከጥቅምት 22- ህዳር 22 2014 ዓ.ም ደግሞ በበይነመረብ ይደረጋል ተብሏል፡፡

አዘጋጆቹ ፕራና ኤቨንትስ እና መቀመጫውን ሱዳን ያደረገው ኤክስፖ ቲም በዛሬዉ እለት እንዳስታወቁት፣ በአዉደርዕዩ ላይ ከተለያዩ ሃገራት የተዉጣጡ የዘርፉ አንቀሳቃሾች ይሳተፉበታል፡፡

አዉደርዕዩ ለዘርፉ አስፈላጊ የሆኑ ቴክኖሎጂዎች የሚቀርቡበት ከመሆኑም ባሻገር ያሉበትን ችግሮች በመፈተሽ መፍትሄ የሚሆኑ ግብዓቶች የሚገኙበት እንደሚሆንም አዘጋጆቹ ተናግረዋል፡፡

ለ3 ቀናት ቆይታ እንደሚኖረዉ የተነገረዉ ይህ አዉደርዕይ በስካይ ላይት ሆቴል የሚካሄድ ሲሆን ከ3 ሺህ በላይ የሚሆኑ ሰዎች ይጎበኙታል ተብሎ እንደሚጠበቅም ኢትዮ ኤፍ ኤም ከአዘጋጆቹ ሰምቷል፡፡

በአዉደርዕዩ ላይም ከኢትዮጵያ፣ ሱዳን፣ ኔዘርላንድስ፣ ጀርመን፣ ሀንጋሪ እና ከሌሎችም ሃገራት የመጡ በዘርፉ የተሰማሩ ኩባንያዎች ይሳተፉበታል ተብሏል፡፡

የዓለም አቀፉ የምግብና እርሻ ድርጅት/ፋኦ/ ሪፖርት እንደሚያመለክተዉ ኢትዮጵያ በ2030 456 ሺህ ቶን የከብት ስጋ፣14 ሺህ 231 ቶን ወተት፣96 ሺህ ዶሮ፣54 ሺህ ቶን እንቁላል እንዲሁም 265ሺህ ቶን የበግና ፍየል ስጋ እንደምትጠቀም ግምቱን አስቀምጧል፡፡

ይሁንና ሃገሪቱ አሁን በዘርፉ ያለባትን ችግር ማሻሻል ካልቻለች ይህን ፍላጎት ለማሟላት እንደምትቸገርም ሪፖርቱ ጠቁሟል፡፡

በሙሉቀን አሰፋ
ጥቅምት 11 ቀን 2014 ዓ.ም

FacebooktwitterredditpinterestlinkedinmailFacebooktwitterredditpinterestlinkedinmail

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *