በዘንድሮው አመት ከ17ሚሊዮን በላይ የሚሆኑ ህፃናት ተጠቃሚ የሚያደርግ የፖሊዮ ክትባት ዘመቻ በኢፌዴሪ የጤና ጥበቃ ሚንስቴር ዴኤታ ዶ/ር ደረጀ ዱጉማ በተገኙበት በይፋ ተጀመረ

ሃገር አቀፍ የፖሊዮ ክትባት ዘመቻ በጌዴኦ ዞን በዲላ ከተማ በኢፌዴሪ የጤና ጥበቃ ሚንስቴር ዴኤታ ዶ/ር ደረጀ ዱጉማ በተገኙበት በይፋ ተጀምሯል ።

በመረሃ ግብሩ በመገኘት ንግግር ያደረጉት የኢፌዴሪ የጤና ጥበቃ ማኒስቴር ዴኤታ ደረጃ ዱጉማ ዶ/ር በወቅቱ እንደተናገሩት የህብረተሰቡን የጤና ስርዓት ለመጠበቅ በትኩረት ይሰራል ብለዋል ።

በሀገር አቀፍ ደረጃ ከጥቅምት 12 እስከ 15/2014 ዓ.ም ድረስ በሚቆየው በቤት ለቤት የፖሊዮ ክትባት ዘመቻ ከ17 ሚሊዮን በላይ ህጻናት የፖሊዮ በሽታ ክትባት እንደሚያገኙ ዶ/ር ደረጀ ገልጸዋል ።

ዕድሜያቸው ከአምስት አመት በታች የሆኑ ህጻናት የሚከተቡበት ሃገር አቀፊ የፖሊዮ ክትባት ዘመቻ በሁሉም አካባቢ ለማድረስ የተለያዩ ባለሙያዎች መዘጋጀታቸውን ዶ/ር ደረጀ ዱጉማ ገልጸዋል ።

በመርሃ ግብር ላይ የፈደራል ጤና ጥበቃ ሚንስቴር ደኤታ ዶ/ር ደረጀ ዱጉማ፤የደቡብ ክልል ጤና ቢሮ ኃላፊ አቶ እንዳሻዉ ሽብሩና የጌዴኦ ዞን ዋና አስተዳዳሪ ጨምሮ የዞንና የወረዳ ከፍተኛ የስራ ሃላፊዎች በተገኙበት በይፋ መጀመሩን የዘገበዉ የጌዴኦ ዞን የመንግስት ኮምኒኬሽን ጉዳዮች መምሪያ ነዉ።
አባቱ መረቀ
ጥቅምት 12 ቀን 2014 ዓ.ም

FacebooktwitterredditpinterestlinkedinmailFacebooktwitterredditpinterestlinkedinmail

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *