ማንነታቸው ያልታወቁ ወታደራዊ ሃይሎች ዛሬ ጠዋት የጠቅላይ ሚኒስትሩን መኖሪያ ቤት በመክበብ ቁጥጥር ስር እንዳዋሏቸው አልጄዚራ በሰበር ዜናው አስነብቧል ።
ከጠቅላይ ሚኒስትሩ በተጨማሪም ሌሎች የካቢኔ አባላት የቤት እስረኛ ስለመሆናቸው ተሰምቷል ።
በአሁኑ ሰዓት የካርቱም መዲናዎች በወታደሮች መዘጋታቸውም ታውቋል።
ከዚህ በተጨማሪ የስልክ ሌሎች መሠረት ልማቶችም አገልግሎት ባለመስጠታቸው በአገሪቱ እየሆነ ያለውን ለማወቅ እንዳልተቻለ አልጄዚራ ዘግቧል ።
ሱዳን ከቅርብ ጊዚያት ወዲህ አስቸጋሪ ሁኔታ ውስጥ እንደምትገኝ የሚታወስ ነው።
ጥቅምት 15 ቀን 2014 ዓ.ም
ኢትዮ ኤፍ ኤም 107.8











