የዓለም አቀፍ ቀይ መስቀል ኮሚቴ (ICRC) በትግራይ ክልል እያደረገ ያለውን እንቅስቃሴ፤ ለማሳለጥ የነዳጅ ፍላጎታቸው እንዲሟላላቸው የመንግስትን ድጋፍ ጠየቁ

የዓለም አቀፍ ቀይ መስቀል ኮሚቴ (ICRC) ፕሬዚዳንት ፒተር ሞረር በዛሬው እለት ከምክትል ጠ/ሚ እና የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር አቶ ደመቀ መኮንን ጋር በጽህፈት ቤታቸው መወያየታቸውን የውጭ ጉዳይ ሚንስቴር አስታውቋል፡፡

የተቋሙ ፕሬዝዳንት በውይይታቸው ወቅት እንዳሉት በኢትዮጵያ ባለው የረጅም ጊዜ አገልግሎት በመንግስት በኩል እየተደረገለት ስላላው ድጋፍ ምስጋና አቅርበው፣ ተቀቋሙ በትግራይ ክልል እያደረገ ያለውን እንቅስቃሴ ለማሳለጥ የነዳጅ ፍላጎታቸው እንዲሟላላቸው፣ የጥሬ ገንዘብ መጠን እንዲጨመር እና የአየር በረራ ፈቃድ እንዲሰጣቸው መንግስትን መጠየቃቸው ተሰምቷል፡፡

አቶ ደመቀ መኮንን በበኩላቸው ICRC በአገራት የውስጥ ጉዳይ ጣልቃ ሳይገባ ፤ በሰብዓዊነት መርህ ተልዕኮውን ለመወጣት እየሰጠ ስላለው አገልግሎት ምስጋና አቅርበዋል፡፡

ድርጅቱ በትግራይ ክልል እያደረገ ካለው የሰብዓዊ ድጋፍ ጋር ተያይዞ በትክክለኛ ፍላጎት ላይ በመመስረት የነዳጅ ሆነ የጥሬ ገንዘብ ፍላጎት እንዲሟላ ከሚመለከታቸው አካላት ጋር በመነጋገር መፍትሄ እንደሚሰጥ አረጋግጠዋል፡፡

አቶ ደመቀ ፤ ” ህወሓት በከፈተው ወረራ ምክንያት ድጋፍ ለሚያስፈልጋቸው እና በተለያዩ የኢትዮጵያ ክፍሎች የሰብዓዊ ዕርዳታ ለሚፈልጉ ዜጎችን ተጨማሪ የሰብዓዊ ድጋፍ ማድረግ አስፈላጊ ነውም” ሲሉ አስረድተዋል።

በተጨማሪ በሰሜኑ የኢትዮጵያ ክፍል ካለው ግጭት ጋር ተያይዞ ያሉትን የጦር እስረኞች በተመለከተ “ታሳሪዎቹ ዜጎቻችን ከመሆናቸውም ባሻገር የዓለም አቀፍ ህግን ታሳቢ በማድረግ ተገቢው አያያዝ ይደረግላቸዋል ” ብለዋል።

ኢትዮ ኤፍ ኤም 107.8 የኢትዮጵያውያን
ጥቅምት 17 ቀን 2014

FacebooktwitterredditpinterestlinkedinmailFacebooktwitterredditpinterestlinkedinmail

Leave a Reply

Your email address will not be published.