ቫይረሱ በደማቸው ከሚገኝ ከ 622 ሺህ በላይ ዜጎች ውስጥ 23 ከመቶዎቹ የፀረ ኤች አይቪ መድሃኒት አይወስዱም ተባለ!!

Posted Leave a commentPosted in የሀገር ውስጥ ዜና

በአሁን ወቅት 622 ሺህ 236 ሰዎች ከቫይረሱ ጋር እንደሚኖሩ ና ከእነዚህ ዜጎች ዜጎች ውስጥ 23 ከመቶ ገደማዎቹ የፀረ ኤች አይቪ መድሃኒት እንደማይወስዱ የፌደራል ኤች አይ ቪ ኤድስ መከላከያና መቆጣጠሪያ ጽ/ቤት የዘርፈ ብዙ ምላሽ ማስተባበሪያ ዳይሬክቶሬት ዳይሬክተር አቶ ክፍሌ ምትኩ ተናግረዋል። ሃላፊው ይህን ያሉት በዛሬው እለት በዓለም አቀፍ ደረጃ “አገልግሎቱን ለተጠቃሚዎች በእኩልነት ተደራሽ ማድረግ ” በሚል […]

የአሸባሪው ህወሓት አባላት እጅ እንዲሰጡ ጠቅላይ ሚኒስትር አብይ ጠየቁ

Posted Leave a commentPosted in የሀገር ውስጥ ዜና

ለአሸባሪው ህወሓት የተሰለፉ ሁሉ እጃቸውን በሰላም እንዲሰጡ ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ አሳስበዋል ለአሸባሪው ዓላማ የተሰለፉ ሁሉ እጃቸውን በመስጠት ራሳቸውን እንዲያተርፉ፣ የትግራይ ወላጆችም ልጆቻችን የት ደረሱ ብለው እንዲጠይቁ ጠቅላይ ሚኒስትሩ ጥሪ አቅርበዋል። በግንባር ተገኝተው በአንደኛው የጦር ግንባር የመጨረሻ ዕቅድ ላይ የመከሩት ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ በአጠረ ጊዜና በአነስተኛ መሥዋዕትነት የኢትዮጵያ ድል የሚረጋገጥበትን መመሪያ ሰጥተዋል። ሠራዊቱ በከፍተኛ ሞራል […]

በደቡብ አፍሪካ ምእራባዊያንን የሚያወግዝ ሰልፍ ሊካሄድ ነው፡፡

Posted Leave a commentPosted in የሀገር ውስጥ ዜና

በደቡብ አፍሪካ የሚኖሩ አፍሪካዊያን በኢትዮጵያ የውስጥ ጉዳይ ላይ እየታየ ያለውን የምእራባውያንን ጣልቃ ገብነትን ለማውገዝ በደቡብ አፍሪካ የሚገኙ ኢትዮጵያውያንና ትውልደ ኢትዮጲያውያንን ጨምሮ ሁሉም የአፍሪካ ሃገራት የሚሳተፉበት ሰልፍ ሊካሄድ ነው፡፡ በደቡብ አፍሪካ በሚገኙ ዋና ዋና ከተሞች ሊካሄድ የታቀደው ሰልፉ መጪው ሰኞ (November 29 ) የሚካሄድ ሲሆን በደቡብ አፍሪካ የኢትዮጵያ ማህበረሰብ ህብረት በሰጠው መግለጫ በእለቱ በሰልፉ የሚታደሙ አፍሪካውያን […]

ደቡብ አፍሪካ ከአስር አመታት በላይ ያስቆጠረው ከ 2 ሺ በላይ ለሚሆኑ የዚምባብዌ ዜጎች የመኖሪያ ና የስራ ፈቃድ እንዲያገኙ የሚፈቅደውን መርሃ ግብር ማዘጋጀቷን ብሉምበርግ ዘግቧል።

Posted Leave a commentPosted in የውጭ ዜና

መርሃ ግብሩ ከጥቅት ወራት በፊት በሀገሪቱ ካቢኔ ባጸደቀውና ጥብቅ የድንበር ቁጥጥር እንዲደረግ የሚያዝዘው ህግ በፈረንጆቹ ዓመት መገባደጃ በኋላ ተግባራዊ ስለሚደረግ እንደሆነ በዘገባው ተጠቅሷል። ካቢኔው የዚምባብዌ ዜጎች እንዲቆዩ ከተፈለገ፣ ለተለያዩ ቪዛዎች ማመልከት እንዳለባቸው፣ካልሆነ ግን ከ12 ወራት በኋላ ከአገር እንደሚባረሩ ካቢኔው ገልጿል። ደቡብ አፍሪካ ወደ 60 ሚሊዮን የሚጠጋ ሕዝብ ያላት ሲሆን፣ ከእነዚህ ውስጥ 3 ሚሊዮን ያህሉ ስደተኞች […]

የአቃቂ ቃሊቲ ክፍለ ከተማ ፖሊስ ከህብረተሰቡ በደረሰው ጥቆማ ለሽብር ተግባር ሊውሉ የነበሩ ቁሳቁሱች መያዙን አስታውቋል፡፡

Posted Leave a commentPosted in የሀገር ውስጥ ዜና

የክፍለ ከተማው ፖሊስ ከሌሎች የፀጥታ ሀይሎች ጋር ባደረገው የተቀናጀ ፍተሻ የነፍስ ወከፍ መሳሪያዎች፣ የብሬል ጥይቶች፣ የአጭር ርቀት መገናኛ ሬድዮኖች እንዲሁም የጦር ሜዳ መነፅርና ተጥለው የተገኙ ቦምቦች ጨምሮ በግለሰብ እጅ መገኘት የሌለባቸው መሳሪያዎችን በቁጥጥር ስር ማዋሉን አስታውቋል፡፡ በተጨማሪም የሽብር አባላት መመልመያ እና ማሰልጠኛ ሰነዶች የተገኙ ሲሆን በተለይም የአሸባሪው ህወሃት ጁንታ መታወቂያና በሽብር ቡድኑ መሪ የተፈረመ የምስክር […]

በአትላስ ሆቴል ለሶስት ዓመታት አልጋ ተከራይቶ የሽብር ድርጊት ሲፈጽም የነበረ ተጠርጣሪ በቁጥጥር ስር ዋለ

Posted Leave a commentPosted in የሀገር ውስጥ ዜና

በአዲስ አበባ ከተማ በቦሌ ክፍለ ከተማ ወረዳ 02 በሚገኘው አትላስ ሆቴል ውስጥ ለሶስት ዓመታት አልጋ ተከራይቶ የሽብር ድርጊት ሲፈጽም የነበረ ተጠርጣሪ በቁጥጥር ስር ዋለ። የኢዜአ ምንጮች እንዳመለከቱት ተጠርጣሪው ከሽብርተኛው ሸኔ ጋር በህቡዕ በመገናኘት ተልዕኮዎችን ሲያስተባብር ነበር፡፡ ተጠርጣሪው ባረፈበት ሆቴል ውስጥ በተደረገ ድንገተኛ ፍተሻ አደንዛዥ ዕፅ፣ ሶስት ኮምፒዩተሮች፣ ሁለት ፕሪንተሮች፣ ሰባት የተለያዩ ማህተሞች፣ አንድ ላፕቶፕ እና […]

የደህንነት ስጋት ናቸው’ ተብለው በቁጥጥር ስር የዋሉትን ተጠርጣሪዎች ከእስር የለቀቁት የደብረብርሀን ከተማ ፖሊስ ፅህፈት ቤት ኃላፊ በቁጥጥር ስር መዋላቸው ተነገረ

Posted Leave a commentPosted in የሀገር ውስጥ ዜና

‘የደህንነት ስጋት ናቸው’ ተብለው በቁጥጥር ስር የዋሉትን ተጠርጣሪዎች ከእስር በመፍታት የተጠረጠሩት የደብረብርሀን ከተማ ፖሊስ ፅህፈት ቤት ኃላፊ ኮማንደር ታዬ ሀብተጊዮርጊስ በዛሬው እለት በቁጥጥር ስር መዋላቸውን ሰማን። የከተማው ሰላምና ደህንነት ፅህፈት ቤት ኃላፊ ዳንኤል እሸቴ ለፋብኮ እንደገለፁት የፖሊስ ፅህፈት ቤት ኃላፊው በቁጥጥር ስር የዋሉት ከአሸባሪው ሕወሓት ጋር ግንኙነት አላቸው ተብለው በቁጥጥር ስር የዋሉ ግለሰቦችን ያለ ኮማንድ […]

የፈረንሳይ መንግስት በኦሮሚያ ክልል በቦረና አካባቢ በድርቅ ለተጎዱ የህብረተሰብ ክፍሎች 1 ሚሊዮን 76 ሺህ 687 ዶላር ድጋፍ አደረገች።

Posted Leave a commentPosted in የሀገር ውስጥ ዜና

በቦረና ዞን በተከሰተው ድርቅ ምክንያት የሞቱ እንስሳት ቁጥር ከ70 ሺ ማለፉን በድርቁ ሳቢያ ከእንስሳት ሞት ባሻገር በሰዎች ህይወት ላይ ማህበራዊ ጉዳት እያደረሰ መሆኑንም ይታወቃል። እስከባላፈው ሳምንት ድረስ 70,185 ከብቶች ሞተዋል ፤ 117,462 እራሳቸው መነሳት የማይችሉ በሰው ድጋፍ የሚነሱ ናቸው ሲሉ የዞኑ አርብቶ አደር ልማት ኃላፊ ዶ/ር ቃሲም ጉዮ ማስታወቃቸው ይታወሳል። ድርቁ እንስሳት ላይ እያደረሰ ካለው […]

የኢትዮጵያ ኤሌክትሪክ ኃይል በ2014 በጀት ዓመት የመጀመሪያዎቹ ሦስት ወራት 3 ሺህ 898 ጊጋ ዋት ሰዓት ኃይል ማመንጨቱን በተቋሙ የኃይል ማመንጫዎች ኦፕሬሽን ሥራ አስፈፃሚ አስታወቁ፡፡

Posted Leave a commentPosted in የሀገር ውስጥ ዜና

ሥራ አስፈፃሚው አቶ እያየሁ ሁንዴሳ እንደገለጹት በ2014 በጀት ዓመት የመጀመሪያ ሩብ ዓመት 4 ሺህ 783 ጊጋ ዋት ሰዓት የኤሌክትሪክ ኃይል ለማመንጨት ታቅዶ 3 ሺህ 898 ጊጋ ዋት ሰዓት ኃይል ማመንጨት ተችሏል፡፡ ‹በበጀት ዓመቱ ማመንጨት ከተቻለው ውስጥ 3 ሺህ 778 ነጥብ 5 ጌጋ ዋት ሰዓት ከውሃ፣ 108 ነጥብ 4 ጌጋ ዋት ሰዓት ከንፋስ እንዲሁም 10 ነጥብ […]

ለአፈር ማዳበሪያ ማስተናገጃነት እንዲውሉ ታስቦ በሞጆ ወደብ የባቡር ተርሚናል አቅራቢያ የተገነቡት ሁለት መጋዘኖች ግንባታቸው ተጠናቆ ለአገልግሎት ዝግጁ መሆናቸው ተገለጸ፡፡

Posted Leave a commentPosted in የሀገር ውስጥ ዜና

ከጅቡቲ በባቡር ተጓጉዘው ለሚገቡ ብትን ጭነቶች በተለይ ለአፈር ማዳበሪያ ማስተናገጃነት እንዲውሉ ታስቦ በሞጆ ወደብ የባቡር ተርሚናል አቅራቢያ የተገነቡት ሁለት መጋዘኖች ለአገልግሎት ዝግጁ መሆናቸውን የኢትዮጵያ ባህር ትራንስፖርት ና ሎጅስቲክስ ድርጅት ነው ያስታወቀው፡፡ K-span በተባለ የግንባታ ቴክኖሎጂ በከፍተኛ ጥራትና ፍጥነት ተገንብተው ለአገልግሎት ዝግጁ የሆኑት እነዚህ ሁለት መጋዘኖች ከ98 ሚሊዮን ብር በላይ ወጪ ተደርጎባቸዋል፡፡ መጋዘኖቹ እያንዳንዳቸው 1ሺ 6 […]