አልጄርያ ወደ ሞሮኮ ጋዝ መላክ አቆመች

በሁለቱ ሀገራት መካከል ባለው ግጭት ምክንያት ወደ ሞሮኮ የምትልከውን ጋዝ ማቆሟን አልጄርያ በፕሬዝዳንት ፅ/ቤት በኩል ገልፃለች፡፡

የሞሮኮ ጠበኛ ባህሪይ የሀገራችንን ብሔራዊ አንድነት የሚሸረሽር ስለሆነ ምንም አይነት ንግድ ከሞሮኮ ጋር አይኖረንም ብለዋል፡፡

ሶናትራች የተባለው የጋዝ ኩባንያ ከሞሮኮው የኤሌክትሪክ ኩባንያ ONEE ጋር ያለውን የንግድ ግንኙነት እንዲያቆም በፕሬዝዳንቱ ታዟል፡፡

ይሄ የማግሬብ-አውሮፓ የጋዝ ቧንቧ የአልጄርያን የተፈጥሮ ጋዝ ተሸክሞ በሞሮኮ አድርጎ እስከ ስፔን ይደርሳል፡፡

ለስፔን በሜድጋዝ ማስተላለፊያ ቧንቧ በኩል ጋዝ ማቅረቧን እንደምትቀጥል አልጄርያ ገልፃች፡፡

አልጄርያ ሞሮኮን የምትከስበት ዋነኛ ምክንያት የአልጄርያን ተገንጣዮች ትረዳለች በሚል ነው፡፡

በተለይ የእስራኤል ቴክኖሎጂዎች በመጠቀም የአልጄርያን ባለስልጣናት ትሰልላለች ስትል ትከሳለች፡፡

ቢቢሲ

ሔኖክ አስራት
ጥቅምት 22 ቀን 2014 ዓ.ም

FacebooktwitterredditpinterestlinkedinmailFacebooktwitterredditpinterestlinkedinmail

Leave a Reply

Your email address will not be published.