በአማራ ክልል በሚደረገዉ ጦርነት ምክንያት ከ6 ሚሊዮን በላይ ህዝብ ለርሀብ መጋለጡን የክልሉ አደጋ መከላከል፣ ምግብ ዋስትናና ልዩ ድጋፍ የሚሹ አካባቢዎች ማስተባበሪያ ኮሚሽን አስታወቀ።

ኮሚሽነር ዘለዓለም ልጃለም ዛሬ በሰጡት መግለጫ እንዳሉት ጦርነት በሚደረግበት በዋግኽምራ ብሔረሰብ አስተዳደር ዝቋላና ጋዝጊብላ ወረዳዎች ብቻ በምግብ፣ በመጠጥ ውሀና በመድኃኒት እጥረት 13 ሰዎች ሞተዋል።

አቶ ዘላለም «ጠላት» ያሉት ሕዝባዊ ወያኔ ሓርነት ትግራይ (ሕወሓት) ሰሜን ወሎ መቄት ወረዳን በያዘበት ወቅት 90 ሰዎችና 13 ወላዶች በመድኃኒትና በሌሎች ግብዓቶች እጥረት ሕይወታቸው እንዳለፈ ገልፀዋል፡፡

ጦርነቱን በመሸሽ ከቤት ንብረቱ የሚፈናቀለው ሰው ቁጥርም ከጊዜ ወደ ጊዜ እየጨመረ መሆኑን ኮሚሽነሩ ጠቅሰዉ የተፈናቃዩ ቁጥር ከአንድ ሚሊዮን መልጡን አስታዉቀዋል።

ኮሚሽነሩ እንደሚሉት የአንዳድ አካባቢ ነዋሪዎች እስከ 4 ጊዜ ለመፈናቀል ተገድደዋል።

በኢትዮጵያ የዩናይትድ ስቴትስ ኤምባሲ፣ የዓለም የህፃናት መርጃ ድርጅት ( UNICEF) የዓለም ምግብ ፕሮግራም (WFP)፣ የአሜሪካ ተራድኦ ድርጅት (USAID)፣ የተባበሩት መንግስታት የሰብአዊ ጉዳዮች ማስተባበሪያ ቢሮ (UNOCHA)፣ ዓለም አቀፍ ቀይመስቀል ማህበር (RED CROSS) እና ሌሎችም ዓለምአቀፍ ረጂ ድርጅቶች በጦርነት ቀጠና ላሉ ወገኖች እርዳታ ለማቅረብ ከክልሉ ከፍተኛ ባለስልጣናት ጋር ተደጋጋሚ ውይይቶችን ያደረጉ ቢሆንም እስካሁን ግን ለሕዝቡ ርዳታ አለመስጠታቸዉን አቶ ዘላለም አስታዉቀዋል።

ኢትዮ ኤፍ ኤም 107.8 የኢትዮጵያውያን
ጥቅምት 25 ቀን 2014 ዓ.ም

FacebooktwitterredditpinterestlinkedinmailFacebooktwitterredditpinterestlinkedinmail

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *