የአቢሲኒያ ባንክ ማየት ለተሳናቸው ሰዎች በድምጽ የሚመራ የኤቲኤም አገልግሎት መስጠት ጀመረ

የአቢሲኒያ ባንክ ማየት ለተሳናቸው ሰዎች የመጀመሪያውን በድምጽ የሚመራ አውቶማቲክ ቴለር ማሽን (ኤቲኤም) አገልግሎት ዛሬ አስተዋውቋል።

በስድስት ኪሎ አካባቢ በሚገኘው የኢትዮጵያ ዓይነ ሥውራን ብሔራዊ ማኅበር ዋና መሥሪያ ቤት የቴክኖሎጂው ሥራ በይፋ መጀመሩን አስታውቋል።

ብዙን ጊዜ በባንክ ሰርአቱ ውስጥ ማየት ለተሳናቸው ሰዎች ተስማሚ ዘዴ ባለመኖሩ ገንዘባቸውን ከባንክ ለማውጣት ይቸገራሉ።

አሁን ግን ከ20 በላይ የአቢሲኒያ ባንክ የኤቲኤም ማሽኖች ያለእርዳታ ገንዘብ ማውጣት ይችላሉ ተብሏል።

ኢትዮ ኤፍ ኤም 107.8 የኢትዮጵያውያን
ጥቅምት 25 ቀን 2014 ዓ.ም

FacebooktwitterredditpinterestlinkedinmailFacebooktwitterredditpinterestlinkedinmail

Leave a Reply

Your email address will not be published.