የአውሮፓ ህብረት በኢትዩጵያ ምንም አይነት ወታደራዊ መፍትሄ እንደሌለ ባወጣው መግለጫ አስታውቋል፡፡

በግጭቱ ውስጥ ያሉ ሁሉም ወገኖች ትርጉም ያለው የተኩስ አቁም በአስቸኳይ ተግባራዊ እንዲያደርጉ እና ፖለቲካዊ ድርድር እንዲጀምሩ ጥሪ አቅርቧል።

ከአንድ አመት ጦርነት በኋላ በሰሜን ኢትዮጵያ ያለው ግጭት የበለጠ ተባብሶ እና እየሰፋ ሄዶ አስከፊ የሆነ ሰብአዊ ቀውስ ፈጥሯል፣ የግዛት አንድነት እና መረጋጋትን በማዳከም በሀገሪቱን አጠቃላይ ተጽእኖ አሳድሯል ነው ያለው።

የአውሮፓ ህብረት ሲያክልም በተለይ ሰሞኑን በአማራ ክልል እየተባባሰ የመጣውን ጦርነት እና የህወሀት እና የኦሮሞ ነጻነት ሰራዊት ወታደራዊ ግስጋሴ እንዲሁም የኢትዮጵያ አየር ሃይል በመቀሌ የአየር ሃይል የቦምብ ጥቃት ሀገሪቱን የበለጠ ሊጎትት ይችላል ብሏል፡፡

ይህም ሀገሪቱን ወደ መከፋፈል እና ሰፊ የትጥቅ ግጭት ከመክተቱም በላይ ህዝቡንም ለባሰ ችግር ያጋልጣል ሲል ባወጣው መግለጫ አሳስቧል፡፡

ያይኔአበባ ሻምበል
ጥቅምት 25 ቀን 2014 ዓ.ም

FacebooktwitterredditpinterestlinkedinmailFacebooktwitterredditpinterestlinkedinmail

Leave a Reply

Your email address will not be published.