የገንዘብ ሚኒስቴር በ100 ቀን 134.6 ቢሊዮን ብር ገቢ ለመሰብሰብ የሚያስችለውን ዕቅድ አወጣ::

“ኢትዮጵያ የተደቀነባትን የህልውና አደጋ ለማስወገድ ከምታደርገው ተጋድሎ በተጓዳኝ ልማታችን ለአፍታም መዘንጋት የለበትም” በማለት የገንዘብ ሚኒስቴር የ100 ቀናት እቅድ አውጥቶ የተለያዩ የኢኮኖሚ ልማት እንቅስቃሴዎችን በማከናወን ላይ እንደሚገኝ አሳወቀ።

በመሆኑም በዛሬው እለት የሀብት አቅርቦትን በማሳደግ የሀገር ውስጥና የውጭ ሀብት በማሰባሰብ እንዲሁም ማክሮ ኢኮኖሚውን ለማረጋጋት በ100 ቀናት ውስጥ የሚከናወኑትን ተግባራት አሳይቷል።

በዚህም ከጠቅላላ የሀገር ውስጥ ገቢ 134.6 ቢሊዮን ብር ገቢ ለመሰብሰብ የታቀደ ሲሆን ከውጭ ሀብት 707 ሚሊዮን ዶላር ፍሰት ይገኛል ተብሎ ታቅዷል፡፡

በዋጋ ግሽበት ላይ በመስራት ማክሮ ኢኮኖሚውን ለማረጋጋት በሚልም በዋና ዋና የምግብ ሸቀጣ ሸቀጦች ላይ ተጥሎ የነበረውን የጉምሩክ ቀረጥና ታክስ ከማንሳት ጀምሮ የተለያዩ ጥረቶች ሲደረግ መቆየቱ የተጠቀሰ ሲሆን በ100 ቀናት የሚኒስቴሩ እቅድም ማክሮ ኢኮኖሚውን ማረጋጋት ተግባር ትኩረት ተሰጥቶታል፡፡

ኢትዮ ኤፍ ኤም 107.8 የኢትዮጵያውያን
ጥቅምት 26 ቀን 2014 ዓ.ም

FacebooktwitterredditpinterestlinkedinmailFacebooktwitterredditpinterestlinkedinmail

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *