ዳሽን ባንክ ገንዘብ በቀላሉ ለመላክ የሚያስችለውን ስምምነት ተፈራረመ

ዳሸን ባንክ ቱንስ ከተባለ አለም አቀፋዊ የክፍያ ኔትዎርክ ኩባንያ ጋር በዛሬው እለት ተፈራርሟል፡፡

ስምምነቱ ደንበኞች ከተለያዩ የአለማችን ክፍሎች የሚላክላቸውን ገንዘብ በቀላሉ ለመቀበል የሚያስችላቸው እንደሆነ የባንኩ ዋና ስራ አስፈጻሚ አቶ አስፋው አለሙ ተናግረዋል፡፡

ባንኩ እንደ ዘመኑ የተለያዩ በዘርፉ የሚያገለግሉ የቴክኖሎጂ አማራጮችን እየተጠቀመ እንደሚገኝ የገለጹት ሀላፊው ስምምነቱ በተለይ ከውጭ ወደ ኢትዮጵያ ገንዘብ በአጭር ጊዜና በተመጣጣኝ ዋጋ ለመላክ ያስችላል ብለዋል።

ስለሆነም በዚሁ አማራጭ ደንበኞች በባንክ ሂሳባቸው ወይም በአሞሌ የሞባይል ዋሌት በኩል ከውጭ የሚላክላቸውን ገንዘብ በአጭር ጊዜ ውስጥ መቀበል ይችላሉ ብለዋል።

የቱንስ ኩባንያ የአፍሪካ ተቀዳሚ ምክትል ፕሬዝደንት የሆኑት ሳንድራ ያኦ በበኩላቸው ስምምነቱ ከተለያዩ የአለም ጫፍ የሚገኙ ሁሉም ደንበኞች በፈጠነ አግባብ ለመላክና ለመቀበል ስለሚኖረው ፋይዳም ተናግረዋል።

ዳሽን ባንክ ከተቋቋመበት እአአ ከ1995 ጀምሮ በመላው ሀገሪቱ ከ460 በላይ ቅርንጫፎቹ መደበኛና ከወሊድ ነጻ አገልግሎት እየሰጠ እንደሚገኝ ከባኩ ገኘው መረጃ ያመለክታል።

ጅብሪል መሀመድ
ህዳር 02 ቀን 2014 ዓ.ም

FacebooktwitterredditpinterestlinkedinmailFacebooktwitterredditpinterestlinkedinmail

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *