የሱዳን ፈጥኖ ደራሽ ኃይሎች መሪው ጄነራል መሐመድ ሐምዳን ዳገሎ በአል ቡርሃን የተሰጣቸውን አዲስ ኃላፊነት አልቀበልም ማለታቸው ተሰማ

የሱዳን ፈጥኖ ደራሽ ኃይሎች መሪው ጄነራል መሐመድ ሐምዳን ዳገሎ አል ቡርሃን 15 አባላት ያቀፈ አዲስ ሉዓላዊ የሽግግር ምክር ቤት ማቋቋማቸውን ተከትሎና ራሳቸውን መሪ አድርገው በመሾማቸው የተነሳ ቅር የተሰኙት ጄነራሉ የአዲሱ ምክር ቤት ምክትል መሪነት ስልጣን አልቀበልም ማለታቸው ተሰምቷል፡፡

ይህንኑ ሹመት ተከትሎ ምክትሉ ሐምዳን ዳጋሎ ከሁለት ዓመት በፊት በቀድሞው ፕሬዝዳንት አል በሽር አገዛዝ ቁጥጥር ስር የነበሩ የተለያዩ ጥሪቶችን የሚያስመልሰውን ኮሚቴ እንዲመሩ ኃላፊነት ቢሰጣቸውም እንደማይቀበሉት መናገራቸውን የአገሪቱ የዜና ወኪል ሱና ዘግቧል፡፡

ሄሜቲ አዲሱን ኃላፊነት ለምን እንዳልተቀበሉት የጠቀሱት ነገር አለመኖሩን ዘገባው አመልክቷል፡፡

ሄሜቲ የመምራት ኃላፊነቱን አልቀበለውም ያሉት ኮሚቴ፣ ሌተናል ጀነራል አብደልፈታህ አል ቡርሃን መፈንቅለ መንግስት አድርገው የአገሪቱን የሲቪል አስተዳደር በመበተን፣ በመላው ሱዳን የአስቸኳይ ጊዜ አዋጅ ሲያውጁ ካገዷቸው መካከል ነው፡፡

ኢትዮ ኤፍ ኤም 107.8 የኢትዮጵያውያን
ሕዳር 07 ቀን 2014 ዓ.ም

FacebooktwitterredditpinterestlinkedinmailFacebooktwitterredditpinterestlinkedinmail

Leave a Reply

Your email address will not be published.