ህጋዊ ያልሆነ ወይም ፎርጅድ መታወቂያ ይዞ መንቀሳቀስ ከ3 እስከ 10 ዓመት እንደሚያስቀጣ የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር የሰላም እና ፀጥታ ቢሮ አስታውቋል።

የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር የሰላም እና ፀጥታ ቢሮ ከአስቸኳይ ጊዜ አዋጅ ጋር በተያያዘ በመታወቂያ አሰጣጥ ላይ ውይይት አድርጓል።

በውይይቱ የአዲስ አበባ ከተማ የሰላም እና ፀጥታ ቢሮ ኃላፊ ዶ/ር ቀንአ ያደታ የአስቸኳይ ጊዜ አዋጁን መሰረት በማድረግ የጊዜያዊ መታወቂያ አሰጣጥ መመሪያ መዘጋጀቱን ገልፀዋል።

መመሪያው ሰላማዊ እና ፀረ ሰላም ኃይሎችን ለመለየት፣ የሐሰት መታወቂያ የሚሰጡ ግለሰቦችንና ቡድኖችን ለመለየት እንዲሁም የመንግስት የሥራ ኃላፊዎች ሆነው ያለ አግባብ ጊዜያዊ መታወቂያ የሚሰጡትን ለመቆጣጠር ያግዛል ብለዋል።

ዶ/ር ቀነዓ ፥ በአስቸኳይ ጊዜ አዋጁ መሰረት ህጋዊ ያልሆነ ወይም ፎርጅድ መታወቂያ ይዞ መንቀሳቀስ ከ3 እስከ 10 ዓመት ያስቀጣል ያሉ ሱሆን ከህዳር 6 /2014 እስከ ህዳር 15/2014 በሚቆየው የጊዜያዊ መታወቂያ አሰጣጥ ሂደት ማህበረሰቡ መታወቂያ ማውጣት እንዳለበት ተናግረዋል።

የሎጂስቲክ እና የሰው ኃይል ቅድመ ዝግጅት ተካሂዶ አርብ ህዳር 10/2014 በየክፍለ ከተማው ጊዜያዊ መታወቂያ ለማህበረሰቡ ለመስጠት ዝግጅት መጀመሩም ተገልጿል።

ኢትዮ ኤፍ ኤም 107.8 የኢትዮጵያውያን
ሕዳር 08 ቀን 2014 ዓ.ም

FacebooktwitterredditpinterestlinkedinmailFacebooktwitterredditpinterestlinkedinmail

Leave a Reply

Your email address will not be published.