የፀረ ተህዋሲያን መድሃኒቶች በጀርሞች መለማመድ በኢትዮጵያ አሳሳቢ ደረጃ ላይ መድረሱን ጤና ሚኒስቴር አስታወቀ

የጤና ሚኒስቴር ሚኒስትሯ ዶ/ር ሊያ ታደሰ እንዳሉት፣ በኢትዮጵያ በአይን የማይታዩ ጀርሞች በተለይ የፀረ ተህዋሲያን መድሃኒቶችን በመለማመድ የሚከሰተው ችግር አሳሳቢነቱ ከአመት አመት እየጨመረ መቷል ብለዋል።

ሚንስትሯ ይህን ያሉት በአለም ለ7ተኛ ጊዜ እንዲሁም በሀገራችን ለ6ተኛ ጊዜ የሚከበረው የዘንድሮው የፀረ ተህዋሲያን መድሃኒት በጀርሞች መለማመድን በማስመልከት የግንዛቤ ማስጨበጫ ሳምንትን ይፋ ባደረጉበት መድረክ ነው።

ችግሩ አለምአቀፋዊ መሆኑን የገለፁት ሚኒስትሯ መረጃዎችን ጠቅሰው በአለም ላይ ከ700 ሺህ በላይ ሰዎች በየዓመቱ ይሞታሉ ብለዋል።

ጥንቃቄ የሚደረግለት ከሆነና በዚሁ ሁኔታ የሚቀጥል ከሆነ ደግሞ እንደ ፈረንጆቹ በ2050 በአለም ዙሪያ እስከ 250 ሚሊዮን ሰዎች ሊሞቱ ይችላሉ ሲሉ ጥናቶችን ጠቅሰው አስረድተዋል።

በሀገራችን ደግሞ፣ በሰው፣ በእንስሳትና በአካባቢ ለይ ከፍተኛ ጉዳትን እያደረሰ ይገኛል ነው ያሉት። በሀገራችን መድሃኒቶችን በመለማመድ ከሚሞቱት ሰዎች መካከከል ደግሞ በዋናነት የቲቢ፣ የኤችአይቪ፣ የልብና ሌሎችም ታማሚዎች ናቸው ብለዋል።

ከእንስሳት ደግሞ በላሞች ላይ ችግሩ የጎላ እንደሆነም ጠቅሰዋል።

ጀርሞች ለፀረ ተህዋሲያን ተብለው የሚሰጡ የተለያዩ መድሃኒቶችን የሚለማመዱት፣ መድሃኒቶችን በጥንቃቄ አለመውሰድ እንደሆነ ዶ/ር ሊያ ተናግረዋል።

ጅብሪል መሀመድ
ህዳር 09 ቀን 2014 ዓ.ም

FacebooktwitterredditpinterestlinkedinmailFacebooktwitterredditpinterestlinkedinmail

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *