ለአፈር ማዳበሪያ ማስተናገጃነት እንዲውሉ ታስቦ በሞጆ ወደብ የባቡር ተርሚናል አቅራቢያ የተገነቡት ሁለት መጋዘኖች ግንባታቸው ተጠናቆ ለአገልግሎት ዝግጁ መሆናቸው ተገለጸ፡፡

ከጅቡቲ በባቡር ተጓጉዘው ለሚገቡ ብትን ጭነቶች በተለይ ለአፈር ማዳበሪያ ማስተናገጃነት እንዲውሉ ታስቦ በሞጆ ወደብ የባቡር ተርሚናል አቅራቢያ የተገነቡት ሁለት መጋዘኖች ለአገልግሎት ዝግጁ መሆናቸውን የኢትዮጵያ ባህር ትራንስፖርት ና ሎጅስቲክስ ድርጅት ነው ያስታወቀው፡፡

K-span በተባለ የግንባታ ቴክኖሎጂ በከፍተኛ ጥራትና ፍጥነት ተገንብተው ለአገልግሎት ዝግጁ የሆኑት እነዚህ ሁለት መጋዘኖች ከ98 ሚሊዮን ብር በላይ ወጪ ተደርጎባቸዋል፡፡

መጋዘኖቹ እያንዳንዳቸው 1ሺ 6 መቶ ሜትር ስኩዌር ስፋት ያላቸው ሲሆን፣ በአንድ ጊዜ 10 ሺ ሜትሪክ ቶን የአፈር ማዳበሪያ /ብትን ጭነት/ የማስተናገድ አቅም አላቸው፡፡

የመጋዘኖቹ መገንባት ብትን ጭነቶችን በተለይ ማዳበሪያን ከጅቡቲ በባቡር አጓጉዞ በፍጥነት ሀገር ውስጥ ለማስገባት ብሎም ለአርሶአደሩ እስከሚደርስ ድረስ ጊዜያዊ ማቆያና ማከፋፈያ ከመሆን ባለፈ በጅቡቲ ወደብ ለመጋዘን ክፍያ የሚወጣውን የውጭ ምንዛሪ በማዳን ረገድም ከፍተኛ ድርሻ እንደሚኖራቸው የኢትዮጵያ ባህር ትራንስፖርት ና ሎጅስቲክስ ድርጅት ነው ያስታወቀው፡፡

ህዳር 15 ቀን 2014 ዓ.ም
ኢትዮ ኤፍ ኤም 107.8 የኢትዮጵያውያን

FacebooktwitterredditpinterestlinkedinmailFacebooktwitterredditpinterestlinkedinmail

Leave a Reply

Your email address will not be published.