በቦረና ዞን በተከሰተው ድርቅ ምክንያት የሞቱ እንስሳት ቁጥር ከ70 ሺ ማለፉን በድርቁ ሳቢያ ከእንስሳት ሞት ባሻገር በሰዎች ህይወት ላይ ማህበራዊ ጉዳት እያደረሰ መሆኑንም ይታወቃል።
እስከባላፈው ሳምንት ድረስ 70,185 ከብቶች ሞተዋል ፤ 117,462 እራሳቸው መነሳት የማይችሉ በሰው ድጋፍ የሚነሱ ናቸው ሲሉ የዞኑ አርብቶ አደር ልማት ኃላፊ ዶ/ር ቃሲም ጉዮ ማስታወቃቸው ይታወሳል።
ድርቁ እንስሳት ላይ እያደረሰ ካለው ጉዳት በተጨማሪ በማህበራዊ ህይወት ላይ ተፅእኖ እያሳረፈ መሆኑን መዘገባችን ይታወሳል።
የፈረንሳይ መንግስትም በቦረና አካባቢ በድርቅ ለተጎዱ የህብረተሰብ ክፍሎች 1 ሚሊዮን 76 ሺህ 687 ዶላር ድጋፍ ማድረጉንና እርዳታው በአካባቢው በተከሰተው ድርቅ ምክንያት ችግር ውስጥ የሚገኙ ዜጎችን ለመታደግ የተጀመረውን ስራ እንደሚያግዝ በኢትዮጵያ ከፈረንሳይ ኤምባሲ ያገኘነው መረጃ ያመላክታል
ህዳር 15 ቀን 2014 ዓ.ም
ኢትዮ ኤፍ ኤም 107.8 የኢትዮጵያውያን











