የአቃቂ ቃሊቲ ክፍለ ከተማ ፖሊስ ከህብረተሰቡ በደረሰው ጥቆማ ለሽብር ተግባር ሊውሉ የነበሩ ቁሳቁሱች መያዙን አስታውቋል፡፡

የክፍለ ከተማው ፖሊስ ከሌሎች የፀጥታ ሀይሎች ጋር ባደረገው የተቀናጀ ፍተሻ የነፍስ ወከፍ መሳሪያዎች፣ የብሬል ጥይቶች፣ የአጭር ርቀት መገናኛ ሬድዮኖች እንዲሁም የጦር ሜዳ መነፅርና ተጥለው የተገኙ ቦምቦች ጨምሮ በግለሰብ እጅ መገኘት የሌለባቸው መሳሪያዎችን በቁጥጥር ስር ማዋሉን አስታውቋል፡፡

በተጨማሪም የሽብር አባላት መመልመያ እና ማሰልጠኛ ሰነዶች የተገኙ ሲሆን በተለይም የአሸባሪው ህወሃት ጁንታ መታወቂያና በሽብር ቡድኑ መሪ የተፈረመ የምስክር ወረቀቶች መገኘት መቻላቸውን ታውቋል።

ክፍለ ከተማው የኦሮሚያ አዋሳኝና ማስፋፊያ ክፍለ ከተማ እንደመሆኑ በርካታ ፀጉረ ልውጦችን እና ሰርጎ ገቦችን ለመለየት እንዲሁም እነሱ ለእኩይ ሴራቸዉ ልጠቀሙባዉ ያሰቡትን መሣሪያዎች የህብረተሰቡ ጥቆማ አስፈላጊ በመሆኑ የተለመደ ትብብሩን አጠናክሮ ሊቀጥል እንደሚገባ መገለጹን የአቃቂ ቃሊቲ ኮሚኒኬሽን ያወጣው መረጃ ያመክታል፡፡

ህዳር 16 ቀን 2014 ዓ.ም
ኢትዮ ኤፍ ኤም 107.8 የኢትዮጵያውያን

FacebooktwitterredditpinterestlinkedinmailFacebooktwitterredditpinterestlinkedinmail

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *