የደህንነት ስጋት ናቸው’ ተብለው በቁጥጥር ስር የዋሉትን ተጠርጣሪዎች ከእስር የለቀቁት የደብረብርሀን ከተማ ፖሊስ ፅህፈት ቤት ኃላፊ በቁጥጥር ስር መዋላቸው ተነገረ

‘የደህንነት ስጋት ናቸው’ ተብለው በቁጥጥር ስር የዋሉትን ተጠርጣሪዎች ከእስር በመፍታት የተጠረጠሩት የደብረብርሀን ከተማ ፖሊስ ፅህፈት ቤት ኃላፊ ኮማንደር ታዬ ሀብተጊዮርጊስ በዛሬው እለት በቁጥጥር ስር መዋላቸውን ሰማን።

የከተማው ሰላምና ደህንነት ፅህፈት ቤት ኃላፊ ዳንኤል እሸቴ ለፋብኮ እንደገለፁት የፖሊስ ፅህፈት ቤት ኃላፊው በቁጥጥር ስር የዋሉት ከአሸባሪው ሕወሓት ጋር ግንኙነት አላቸው ተብለው በቁጥጥር ስር የዋሉ ግለሰቦችን ያለ ኮማንድ ፖስቱ ፈቃድ ከማቆያ እንዲወጡ አድርገዋል በሚል ነው።

በዚህ ወንጀል የተሳተፉ ሌሎች አመራሮች መኖራቸውን በተመለከተም ከህዝብ ጥቆማዎች እየደረሳቸው እንደሚገኝ የገለጹት የፅህፈት ቤቱ ኃላፊ መረጃውን ለማጥራት እየተሠራ ነውም ብለዋል፡፡

ህዳር 16 ቀን 2014 ዓ.ም
ኢትዮ ኤፍ ኤም 107.8 የኢትዮጵያውያን

FacebooktwitterredditpinterestlinkedinmailFacebooktwitterredditpinterestlinkedinmail

Leave a Reply

Your email address will not be published.