በደቡብ አፍሪካ ምእራባዊያንን የሚያወግዝ ሰልፍ ሊካሄድ ነው፡፡

በደቡብ አፍሪካ የሚኖሩ አፍሪካዊያን በኢትዮጵያ የውስጥ ጉዳይ ላይ እየታየ ያለውን የምእራባውያንን ጣልቃ ገብነትን ለማውገዝ በደቡብ አፍሪካ የሚገኙ ኢትዮጵያውያንና ትውልደ ኢትዮጲያውያንን ጨምሮ ሁሉም የአፍሪካ ሃገራት የሚሳተፉበት ሰልፍ ሊካሄድ ነው፡፡

በደቡብ አፍሪካ በሚገኙ ዋና ዋና ከተሞች ሊካሄድ የታቀደው ሰልፉ መጪው ሰኞ (November 29 ) የሚካሄድ ሲሆን በደቡብ አፍሪካ የኢትዮጵያ ማህበረሰብ ህብረት በሰጠው መግለጫ በእለቱ በሰልፉ የሚታደሙ አፍሪካውያን የ #nomore አለምአቀፍ ህዝባዊ ንቅናቄን በመቀላቀል ለዓለም ህዝብ የቀኝ ግዛት ዘመን እንደማይደገም መልእክታቸውን ለምእራባውያኑ እንደሚስተላልፉ አስታውቀዋል፡፡

አፍሪካዊያን የጋራ የሆኑ ጉዳዮቻችንን በጋራ መፍታት አለብን ብለው የተነሱለት የሰልፉ አስተባባሪዎች ይህንኑ ፓን አፍሪካዊነትን የሚያንፀባርቀው ሰልፍም በዋነነት የሚካሄደው ደቡብ አፍሪካ በሚኖሩ ኢትዮጵያውያን አነሳሽነት መሆኑን ገልፀዋል፡፡

የተለያዩ ሃገራት አፍሪካዊያን ዲያስፓራዎችም ይህንን ሰልፍ እንደሚቀላቀሉ የሚጠበቅ ሲሆን ምእራባውያኑ ሃገራት በኢትዮጲያ የውስጥ ጉዳይም ሆነ በአህጉሪቱ በሚካሄዱ የውስጥ ጉዳዮች ላይ የሚያሳድሩትን ጫና ለማስቆም የሚካሄድ ሰልፍ መሆኑም ተነግሯል፡፡

ህዳር 17 ቀን 2014 ዓ.ም
ኢትዮ ኤፍ ኤም 107.8 የኢትዮጵያውያን

FacebooktwitterredditpinterestlinkedinmailFacebooktwitterredditpinterestlinkedinmail

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *