ደቡብ አፍሪካ ከአስር አመታት በላይ ያስቆጠረው ከ 2 ሺ በላይ ለሚሆኑ የዚምባብዌ ዜጎች የመኖሪያ ና የስራ ፈቃድ እንዲያገኙ የሚፈቅደውን መርሃ ግብር ማዘጋጀቷን ብሉምበርግ ዘግቧል።

መርሃ ግብሩ ከጥቅት ወራት በፊት በሀገሪቱ ካቢኔ ባጸደቀውና ጥብቅ የድንበር ቁጥጥር እንዲደረግ የሚያዝዘው ህግ በፈረንጆቹ ዓመት መገባደጃ በኋላ ተግባራዊ ስለሚደረግ እንደሆነ በዘገባው ተጠቅሷል።

ካቢኔው የዚምባብዌ ዜጎች እንዲቆዩ ከተፈለገ፣ ለተለያዩ ቪዛዎች ማመልከት እንዳለባቸው፣ካልሆነ ግን ከ12 ወራት በኋላ ከአገር እንደሚባረሩ ካቢኔው ገልጿል።

ደቡብ አፍሪካ ወደ 60 ሚሊዮን የሚጠጋ ሕዝብ ያላት ሲሆን፣ ከእነዚህ ውስጥ 3 ሚሊዮን ያህሉ ስደተኞች መሆናቸውን የብሔራዊ ስታቲስቲክስ ኤጀንሲ አስታውቋል።

ህዳር 17 ቀን 2014 ዓ.ም
ኢትዮ ኤፍ ኤም 107.8 የኢትዮጵያውያን

FacebooktwitterredditpinterestlinkedinmailFacebooktwitterredditpinterestlinkedinmail

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *