ቫይረሱ በደማቸው ከሚገኝ ከ 622 ሺህ በላይ ዜጎች ውስጥ 23 ከመቶዎቹ የፀረ ኤች አይቪ መድሃኒት አይወስዱም ተባለ!!

በአሁን ወቅት 622 ሺህ 236 ሰዎች ከቫይረሱ ጋር እንደሚኖሩ ና ከእነዚህ ዜጎች ዜጎች ውስጥ 23 ከመቶ ገደማዎቹ የፀረ ኤች አይቪ መድሃኒት እንደማይወስዱ የፌደራል ኤች አይ ቪ ኤድስ መከላከያና መቆጣጠሪያ ጽ/ቤት የዘርፈ ብዙ ምላሽ ማስተባበሪያ ዳይሬክቶሬት ዳይሬክተር አቶ ክፍሌ ምትኩ ተናግረዋል።

ሃላፊው ይህን ያሉት በዛሬው እለት በዓለም አቀፍ ደረጃ “አገልግሎቱን ለተጠቃሚዎች በእኩልነት ተደራሽ ማድረግ ” በሚል መርህ እየተከበረ ባለው የ ኤድስ ቀን ነው፡፡

የፌደራል ኤች አይ ቪ ኤድስ መከላከያና መቆጣጠሪያ ጽ/ቤት የዘርፈ ብዙ ምላሽ ማስተባበሪያ ዳይሬክቶሬት ዳይሬክተር አቶ ክፍሌ ምትኩ ለኢትዮ ኤፍ ኤም እንዳሉት ፣ በወሲብ ንግድ ላይ የተሰማሩ ሴቶች ፣ የህግ ታራሚዎች እና አንደዛዥ እፅ በመርፌ የሚወስዱ ሰዎች ቀዳሚ የቫይረሲ ተጋላጭ መሆናቸውን ተናግረዋል።

በሌላ በኩል ደግሞ በወሲብ ንግድ ላይ ተሰማርተዋል ተብለው ከሚታሰቡ 210 ሺህ ገደማ ሴቶች ውስጥ የተመረመሩት 113 ሺህ 619 ሲሆኑ ከእነዚህ ውስጥ 3.5 ከመቶዎቹ ቫይረሱ በደማቸው እንደሚገኝ ተረጋግጧል።

በአገር አቀፍ ደረጃ 622 ሺህ 236 ሰዎች ከቫይረሱ ጋር እንደሚኖሩ የተነገረ ሲሆን ከእነዚህ ዜጎች ውስጥ 77.2 በመቶዎቹ የፀረ ኤች አይ ቪ ኤድስ መድሃኒት የሚወስዱ ሲሆን ቀሪዎቹ 23 ከመቶ ገደማዎቹ እንደማይወስዱ ሃላፊው አቶ ክፍሌ ምትኩ ተናግረዋል።

ረድኤት ገበየሁ
ህዳር 21 ቀን 2014 ዓ.ም

FacebooktwitterredditpinterestlinkedinmailFacebooktwitterredditpinterestlinkedinmail

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *