ኢትዮጵያ ችግሯን ያለማንም ጣልቃ ገብነት በራሷ የመፍታት አቅም አላት ሲሉ የቻይናው ውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ተናገሩ

ዛሬ ጠዋት አዲስ አበባ የገቡት የቻይና የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ዋንግ ዩ ከምክትል ጠቅላይ ሚኒስትርና የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር አቶ ደመቀ መኮንን ጋር በሃገራቱ የሁለትዮሽ ግንኙነት እና ወቅታዊ ጉዳዮች ዙሪያ በተወያዩበት ወቅት እንዳሉት ኢትዮጵያ፣ ችግሯን ያለማንም ጣልቃ ገብነት በራሷ የመፍታት አቅም አላት ብለዋል፡፡

የውጭ ጉዳይ ሚንስትሩ ደመቀ መኮንን በበኩላቸው በኢትዮጵያ የተፈጠረውን ጦርነት አስመልክቶ ችግሩን ለመፍታት መንግስት እየሄደበት ያለውን መንገድ ያስረዷቸው ሲሆን ፣ቻይናው አቻቸው በበኩላቸው” የኢትዮጵያና የቻይና ወዳጅነት ጠንካራ እና የማይበጠስ ነው “ብለዋል፡፡

ኢትዮጵያውያን ችግሮቻቸውን በራሳቸው የመፍታትና ሁኔታዎችን የማረጋጋት ጥበብ ስላላቸው ቻይና በኢትዮጵያ የውስጥ ጉዳይ ውስጥ ጣልቃ ለመግባት የሚደረገውን ማንኛውንም ሙከራ ትቃወማለች ብለዋል።

ቻይና ከኢትዮጵያ ህዝብና መንግስት ጋር ያላትን በመርህ ላይ የተመሰረተና ወጥነት ያለው ወዳጅነት ያደነቁት ፣ አቶ ደመቀ ሁሉም ነገር ደህንነቱ በተጠበቀበት እና የሀገሪቱ ሁኔታ የተረጋጋና በቁጥጥር ስር ባለበት ሁኔታ ዋንግ ዪ ወደ አዲስ አበባ በመምጣታቸው ደስተኛ መሆናቸውን ተናግረው ፤ ቻይና ለኢትዮጵያ ሉዓላዊነትና የግዛት አንድነት ያላትን ጠንካራ ቁርጠኝነት አድንቀዋል።

ኢትዮ ኤፍ ኤም 107.8 የኢትዮጵያውያን
ህዳር 22 ቀን 2014 ዓ.ም

FacebooktwitterredditpinterestlinkedinmailFacebooktwitterredditpinterestlinkedinmail

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *