የገቢዎች ሚኒስቴር በበጀት ዓመቱ ለመሰብሰብ ያቀደው ገቢ እንዳይስተጓጎል፣ ጦርነት እየተደረገባቸው ባሉ ቦታዎች ያልተሰበሰበውን ገቢ በሌሎች አማራጮች የማካካስ ዕቅድ እንዳለው አስታውቀ፡፡

የገቢዎች ሚኒስትር ዴኤታ ወ/ሮ መሠረት መስቀሌ፣ ገቢውን ለማካካስ ውዝፍ ዕዳ እንዲከፈል ማድረግን ጨምሮ የተለያዩ መንገዶችን የመጠቀም ሐሳብ እንዳለ ለሪፖርተር ተናግረዋል፡፡

የገቢዎች ሚኒስቴር በአራት ወራት አፈጻጸም ሪፖርቱ ለመሰብሰብ አቅዶ ከነበረው 133 ቢሊዮን ብር ውስጥ፣ 123.9 ቢሊዮን ብር የሚሆነውን መሰብሰቡን አስታውቋል፡፡

ይኼም ዕቅዱ 92 በመቶ መፈጸሙን የሚያሳይ ሲሆን፣ በዕቅዱና በተሰበሰበው ገቢ መካከል የአሥር ቢሊዮን ብር ልዩነት አለ፡፡

ሚኒስትር ዴኤታዋ በአገሪቱ እየተደረገ ያለው ጦርነት በገቢ አሰባሰብ ሒደቱ ላይ ተፅዕኖ ማድረሱ የማይቀር እንደሆነ ተናግረዋል፡፡

የገቢዎች ኮምቦልቻ ቅርንጫፍ እስከ ጥቅምት አጋማሽ ድረስ ገቢ ሲሰበስብ የቆየ መሆኑን የገለጹት ወ/ሮ መሠረት፣ የጥቅምት ወር አፈጻጸሙ ግን 45 በመቶ መሆኑን ጠቁመዋል፡፡

ኢትዮ ኤፍ ኤም 107.8 የኢትዮጵያውያን
ህዳር 22 ቀን 2014 ዓ.ም

FacebooktwitterredditpinterestlinkedinmailFacebooktwitterredditpinterestlinkedinmail

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *