በኢትዮጵያ ቆዳ ኢንዱስትሪዎች ማህበርና የኢትዮጵያ ጨርቃጨርቅና አልባሳት ማህበር አዘጋጅነት ሰባተኛው የመላው አፍሪካ የቆዳ ትርኢትና የፋሽን ምንጭ ሳምንት ዐውደ ርእይ ተከፈተ።

ከ150 በላይ አለም አቀፍ አምራችና ላኪዎች፤ በአለም ላይ ከአራት ሺህ በላይ የንግድ ባለሙያዎች፤ በአፍሪካ የቆዳና ቆዳ ውጤቶች፣ ጨርቃጨርቅና አልባሳት ኤግዚቢሽን ላይ ከተለያዩ የአፍሪካ አገራት፣ ከኤዥያ፣ ከአውሮፓና አሜሪካ የተጋበዙ ድርጅቶች ይሳተፋሉ።

የኢንዱስትሪ ሚኒስቴር ሚኒስትር ዴኤታ አቶ ሺህሰማ ገብረስላሴ በኤግዚቢሽን መክፈቻው ላይ እንደገለጹት፣ኢትዮጵያ በአሁኑ ወቅት ዘመቻ ለህብረ ብሄራዊነት ላይ ትገኛለች፤ ኢትዮጵያ ወንድማማችነትን የምትፈልግ የሌሎችን አገራት ሉአላዊነት የምታከበር ናት ብለዋል።

የኤግዚቢሽኑ ዋና አላማ ጤናማ የንግድ ስርአት እንዲፈጠርና የኢኮኖሚ እድገት እንዲኖር ማድረግ ነው ብለዋል።

ተሳታፊዊችም በአህጉሪቱ ያለውን ነፃ የግብይት ቀጠናን እንዲሁም የተባበሩት መንግሥታትን የልማት ግብ በመጠቀም አፍሪካ በዘርፉ ያላትን አስተዋፅኦ በማሳደግ ረገድ የጎላ ሚና ያበረክታሉ ተብሎ እንደሚጠበቅም የዐውደ ርእዩ አዘጋጆች ገልጸዋል።

የንግድና ቀጠናዊ ትስስር ሚኒስትር ዴኤታ፣ የኢትዮጵያ ቆዳ ኢንዱስትሪዎች ልማት ኢንስቲትዩት ፕሬዚዳንቶች፣ የተባብሩት መንግስታት ተወካዮችና ሌሎች እንግዶች ተገኝተዋል።

ከህዳር 24 እስከ ህዳር 27 በሚቆየው ዐውደ ርእይ ከደቡብ፣ ከምዕራብ እና ከምሥራቅ አፍሪካ የተውጣጡ ከ25 በላይ የሚሆኑ ከፍተኛ የሚባሉ የዘርፉ ፋሽን ዲዛይነሮች የታገዘ መሆኑም ተገልጿል።

ጅብሪል መሀመድ
ህዳር 24 ቀን 2014 ዓ.ም

FacebooktwitterredditpinterestlinkedinmailFacebooktwitterredditpinterestlinkedinmail

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *