የሱዳን ወታደራዊ መንግስት በተባበሩት መንግስታት ድርጅት እገዛ እንዲደረግለት ጠየቀ፡፡

የሱዳኑ ወታደራዊ መንግስት መሪው አብዱል ፈታህ አል ቡሀርሃን በተባበሩት መንግስታት ድርጅት፤ እንደገና የሽግግር መንግስት ለመመስረት በሚደረገው ሂደት እገዛ እንዲደረግላቸው ጥሪ አቅርበዋ፡፡

አልቡርሃን በሀገሪቱ የተባበሩት መንግስታት ድርጅት ልዩ ተወካይ ቮልከር ፔርቴስን ፤ ወደ ስልጣናቸው ከተመለሱት የሲቪል አስተዳደሩ ጠቅላይ ሚኒስትሩ አብደላ ሃምዶክ ጋራ የጋራ የሽግግር መንግስት ለመመሰረት ፈቀዳኛ እንደሆኑ እና በትብብት ለመስራት እንደወሰኑ አስረድተዋል፡፡

አልቡርሃን ያቀረቡትን የእርዳታ ጥሪ በማስመለከት የድርጅቱ ተወካይ በቲዊተር ገፃቸው ላይ እንደተናገሩት፤ ምንም እንኳን ወደ ህገ-መንግስታዊ ስርዓቱ ለመመለስ ስምምነቱን ቢቀበሉም “ሌሎች ወሳኝ እርምጃዎችን መከተል እና ማክበር አስፈላጊ እንደሆነ ምላሽ ሰተዋል፡፡

ባለፈው የጥቅምት ወር በወታደራዊ ሃይሉ የተደረገውን የመንግስት ግልበጣ ተከትሎ በሱዳን የነበረው የሽግግር መንግስቱ መፍረሱ የሚታወስ ነው፡፡

ወታደራዊ መንግስቱን በበላይነት የሚመሩት ጄነራል አብዱል ፈታህ አልቡርሃን ደግሞ የራሳቸውን ጊዚያዊ መንግስት በመመሰረት እራሳቸውን መሪ አደርገው መምረጣቸው አይዘነጋም፡፡

ነገር ግን አልቡርሃን እራሳቸው የመንግስት ግልበጣ አድርገው የመሰረቱት፤ በዜጎች ከፍተኛ ተቃውሞ የገጠመው በመሆኑ መሪው አጣብቂኝ ውስጥ እንደሚገኙ አይዘነጋም፡፡

በዚህም እንደገና ወደ ስልጣን ከመለሷቸው የሲቪል አስተዳደሩ ጠቅላይ ሚስትሩ አብደላ ሃምዶክ እና የወታደራዊ መንግስቱ በጋራ በመሆን እንደገና የሽግግር መንግስት ለመመስረት ሲባል የዩኤንን እርዳታ መጠየቃቸውን ቢቢሲ አፍሪካ አስነብቧል፡፡

ጅብሪል መሀመድ
ህዳር 24 ቀን 2014 ዓ.ም

FacebooktwitterredditpinterestlinkedinmailFacebooktwitterredditpinterestlinkedinmail

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *