እስከ ታህሳስ መጨረሻ ድረስ 400ሺህ ሜትሪክ ቶን እህል ወደ ሀገር ቤት ይገባል ተባለ፡፡

ለተፈናቃይ ወገኖች እየተደረገ ባለው ድጋፍ ላይ እጥረት እንዳይፈጠር መንግስት ከውጪ እህል ገዝቶ እያስገባ መሆኑን የብሄራዊ አደጋ ስጋት ስራ አመራር ኮሚሽን አስታወቀ።

በጦርነቱ ምክንያት ለተፈናቀሉ ዜጎች እየተደረገ ባለው ድጋፍ እጥርት እንዳይፈጠር 400ሺህ ሜትሪክ ቶን እህል ተገዝቶ ወደ ሀገር ውስጥ እየገባ እንደሆነ የአደጋ ስጋት ስራ አመራር ኮሚሽን የህዝብ ግኑኝነት ሀላፊ አቶ ደበበ ዘውዴ ገልጸዋል፡፡

የተገዛው እህልም እስከ ታህሳስ መጨረሻ ድረስ ወደ ሀገር ውስጥ ይገባል ያሉ ሲሆን በተጨማሪም 300ሺህ ሜትሪክ ቶን እህል ግዢ ለማከናንም በሂደት ላይ ነው ብለዋል፡፡

በአሁኑ ሰአት የተፈናቃች ቁጥር ከመጨመሩ ጋር በተያያዘም ድጋፍ የሚሹ ዜጎች ቁጥርም ከፍተኛ ነው ተብሏል፡፡

ለተፈናቃዮች ድጋፍ ማድረግ የሚሹ ድርጅቶች ግለሰቦች እና ረጂ ድርጅቶች ለተፈናቃይ ዜጎች በአግባቡ እንዲደርስ በኮሚሽኑ በኩል ቢያደርጉ የተሸለ ይሆናል ሲሉ አቶ ደበበ ተናግረዋል፡፡

ኢትዮ ኤፍ ኤም 107.8 የኢትዮጵያውያን
ህዳር 28 ቀን 2014 ዓ.ም

FacebooktwitterredditpinterestlinkedinmailFacebooktwitterredditpinterestlinkedinmail

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *