የትራንስፖርት የታሪፍ ማሻሻያ በነገው እለት ይፋ ይደረጋል ተባለ፡፡

ከታህሳሰስ ወር ጀምሮ የነዳጅ ችርቻሮ ዋጋ ላይ ጭማሪ መደረጉ ተከትሎ የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር የትራንስፖርት ቢሮ የታሪፍ ማሻሻያ በነገው እለት ይፋ አደርጋለሁ ብሏል፡፡
የዓለም አቀፍ ነዳጅ ምርቶች መሸጫ ዋጋ እየጨመረ ከመምጣቱ ጋር ተያይዞ የነዳጅ ማረጋጊያ ፈንድ ከመቼውም ጊዜ በላይ ከፍተኛ ጉድለት ያስከተለ መሆኑን ና የአገር ውስጥ የችርቻሮ መሸጫ ዋጋ ከጎረቤት አገራት የችርቻሮ መሸጫ ዋጋ እስከ አንድ መቶ ፐርሰንት በማደጉ ብሎም አገሪቱ ካለችበት ነባራዊ ሁኔታ አንጻር የነዳጅ ምርቶች የችርቻሮ መሸጫ ዋጋ መጨመሩ ይታወቃል፡፡
የከተማ ትራንስፖርት ቢሮ የታሪፍ ማሻሻያ አጥንቶ በነገው እለት ይደረጋል ሲል የቢሮው የኮሙንኬሽን ሃላፊ አረጋዊ ማሩ አስታውቀዋል፡፡

ታህሳስ 07 ቀን 2014 ዓ.ም
ኢትዮ ኤፍ ኤም 107.8 የኢትዮጵያውያን!!!

FacebooktwitterredditpinterestlinkedinmailFacebooktwitterredditpinterestlinkedinmail

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *