በአዲስ አበባ በሚኒባሶች እና ታክሲዎች ላይ ከዛሬ ጀምሮ ተግባራዊ የሚደረግ የታሪፍ ማሻሻያ ይፋ ሆነ፡፡

የአዲስ አበባ ትራንስፖርት ቢሮ በህዝብ ትራንስፖርት አገልግሎት ሰጪ ተሸከርካሪዎች ላይ አጥንቶ አዲስ የታሪፍ ማሻሻያ አድርጓል፡፡

በዚህም መሰረት በሚኒባስ (ቅጥቅጥ ወይም ሃይገር ባስ) የተደረገው የታሪፍ ማሻሻያ በሚኒባስ በኪሎሜትር ከ40 ሳንቲም ወደ 45 ሳንቲም ከፍ የተደረገ ሲሆን÷ በታክሲ ደግሞ በኪሎሜትር ከ90 ሳንቲም ወደ 1 ብር ከፍ ብሏል፡፡

በሚኒባሶች የተደረገው ጭማሪ ዝቅተኛው 1 ብር ሲሆን÷ ከፍተኛው ደግሞ 2 ብር ሆኗል፡፡

በታክሲ ላይ የተደረገው ጭማሪ ዝቅተኛ 50 ሳንቲም ሲሆን ከፍተኛው ጭማሪ 3 ብር ከ50 ሳንቲም መሆኑ ተገልጿል፡፡

ጭማሪው የኪሎሜትር ርቀትን ታሳቢ ያደረገ መሆኑ በመግለጫው ተመላክቷል፡፡

የታሪፍ ጭማሪው በብዙሃን ትራንስፖርት ላይ እንዳልተደረገ የከተማው የትራንስፖርት ቢሮ ዛሬ በመግለጫው አስታውቋል፡፡

ኢትዮ ኤፍ ኤም 107.8 የኢትዮጵያውያን
ታህሳስ 08 ቀን 2014 ዓ.ም

FacebooktwitterredditpinterestlinkedinmailFacebooktwitterredditpinterestlinkedinmail

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *