“ዘመቻ ለኅብረ ብሔራዊ አንድነት” ዓላማውን አሳክቶ በድል መጠናቀቁን የመንግስት ኮሚኒኬሽን አገልግሎት አስታወቀ።
አገልግሎቱ ዛሬ በሰጠው መግለጫ የዘመቻው ዋና ዓላማ የነበረው አሸባሪውንና ወራሪውን የህወሃት ቡድን ከአማራ እና አፋር ክልሎች ጠራርጎ ማውጣት እና አሸባሪ ቡድኑ ለሀገሪቱ ዳግም ስጋት እንዳይሆን ማድረግ ነበር ብሏል።
ዘመቻው ይህንን ሙሉ በሙሉ ማሳካቱን ነው ያመለከተው።
ኢትዮ ኤፍ ኤም 107.8 የኢትዮጵያውያን
ታህሳስ 14 ቀን 2014 ዓ.ም











