በአዲስ አበባ ከተማ የሚገኙ የሜትር ታክሲ አገልግሎት ሰጪ ማህበራት፣ የጠቅላይ ሚንስትሩን ጥሪ ተቀብለው ለገና በዓል ወደ ሀገር ቤት ለሚመጡ የዲያስፖራ አባለት ከዛሬ ጀምሮ የነጻ የትራንስፖርት አገልግሎት ለመስጠት መስማማታቸውን ገልጸዋል፡፡
የአዲስ አበባ ትራንስፖርት ቢሮ በዛሬው እለት በኤሊያና ሆቴል ከታክሲ ማህበራት አመራሮችና አባላት ጋር ውይይት በማድረግ ላይ ናቸው፡፡
በዚህ ወቅት የማህበራቱ ተወካዮች እንዳሉት ወደ ሀገር ቤት ለሚመጡ የዲያስፖራ አባላት ከአየር ማረፊያ እስከ መዳረሻቸው ድረስ የነጻ የትራንስፖር አገልግሎት ለመስጠት መስማማታቸውን ገልጸዋል፡፡
አገልግሎቱ የገና በዓል እስኪጠናቀቅ ድረስ የሚቆይ እንደሆነ ተነግሯል፡፡
መስማማታቸውን የገለጹት ከ45 በላይ የሜትር ታክሲ አገልግሎት ሰጪ ማህበራት እንደሆኑ ታውቋል፡፡
ሔኖክ ወ/ገብርኤል
ታህሳስ 19 ቀን 2014 ዓ.ም











