ኤርፖርት አካባቢ የሚሰሩ የኮድ 3 ባለታክሲዎች ከድርጊታቸው የማይቆጠቡ ከሆነ ስምሪታቸው ይሰረዛል ተብሏል፡፡

ስምሪታቸው ቦሌ ኤርፖርት አካባቢ የሆኑ የኮድ 3 ባለታክሲዎች አብዛኛዎቻቸው በወንጀል ድርጊት ተሳትፎ እያደረጉ ይገኛሉ ሲል ያሳወቀው የአዲስ አበባ ትራንስፖርት ቢሮ ነው፡:

ባለታክሲዎቹ ከወንጀለኞች ጋር በመተባበር ከኤርፖርት ወደ መሀል ከተማ የሚንቀሳቀሱትን ዜጎች እያገቱ የወንጀል ድርጊት እየፈጸሙ ይገኛሎ ያሉት የቢሮው ሀለፊው አቶ ዳዊት የሺጥላ ናቸው፡፡
በቅርቡም የትራንስፖርት አገልግሎት የሚሰጡ በማስመሰል ዜጎችን እየዘረፉ ይገኛሉ ተብሏል፡፡

የአዲስ አበባ ትራንስፖርት ቢሮ ኤርፖርት አካባቢ የትራንስፖርት አገልግሎት ለመስጠት ስምሪት የተሰጣቸው አሽከርካሪዎች ከወንጀለኞች እኩል እየሰሩ ነው ሲል አስታውቋል፡፡
ሀለፊው አቶ ዳዊት የሺጥላ እንደተናገሩት የትራንስፖርት አገልግሎት እየሰጡ እንደሆነ በማስመሰል አብዛኛዎቹ ኮድ3 ባለታክሲዎች በወንጀል ድርጊት ተሳትፎ ያላቸው ናቸው ብለዋል፡፡

ከሰሞኑ ዲያስፖራዎች ወደ ሀገር ቤት ከመግባታቸው ጋር በተያያዘም በስፍራው ሊፈጠሩ የሚችሉ የወንጀል ድርጊቶች ቀድሞ ለመከላከል ኤርፖርት አካባቢ የሚንቀሳቀሱ ኮድ 3 ተሽከርካሪዎች ስምሪታቸው ሊሰረዝ ይችላል ብለዋል፡፡

ዲያስፖራዎቹ ገብተው እስኪጠናቀቁ ድረስም ትራንስፖርት ቢሮው ከአዲስ አበባ ፖሊስ ኮሚሽን ጋር በመተባበር ኤርፖርት አካባቢ የሚንቀሳቀሱ ተሸከርካሪዎች ላይ ከፍተኛ ክትትል እንደሚደረግ ነው የአዲስ አበባ ትራንስፖርት ቢሮ የገለጸው፡፡

ሔኖክ ወ/ገብርኤል
ታህሳስ 20 ቀን 2014 ዓ.ም

FacebooktwitterredditpinterestlinkedinmailFacebooktwitterredditpinterestlinkedinmail

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *