ከኮምቦልቻ እና መቀሌ የገቢዎች ሚኒስቴር እና ጉሩክ ኮሚሽን ከ2.3 ቢሊዮን ብር በላይ ገቢ አለመሰብሰቡን የገቢዎች ሚኒቴር አስታወቀ፡፡

በ2014 በጀት ዓመት 360 ቢሊየን ብር የመሰብሰብ እቅድን አስቀምጦ ሥራ የጀመረው ሚኒስቴሩ ባለፉት አምሰት ዋር 158.9 ቢሊዮን ለመሰብሰብ አቅዶ 147.3 ቢሊየን ሰብስቧ፡፡

ይህም የእቅዱን 92.6 በመቶ ማሳካት መቻሉን መስሪቤቱ አስታውቋል፡፡

የሚኒስቴሩ የኮሙዩኒኬሽን ዳይሬክተር ወ/ሮ ኡሚ አባጀማል የገቢ አፈጻጸሙ በሀገራችን በተከሰተው የጸጥታ መደፍረስ እና የኮቪድ ወረርሽኝ ችግር ውስጥ ሆኖ የተመዘገበ በመሆኑ ስኬታማ ነው ሊባል እንደሚችል ገልፀዋል፡፡

ለዚሁ ስኬት ግብር ከፋዮች፣ የግብር ሰብሰባቢው ተቋም ሰራተኞችን እንዲሁም ሌሎች ባለድርሻ አካላትን ያመሰገኑት ዳይሬክተሯ በአመስቱ ወራት በጸጥታ መደፍረስ ምክንያት በመቀሌ ገቢዎች ሚኒስቴር እና ጉምሩክ ኮምሽን
ቅርንጫፎች በድምሩ 1.8 ቢሊየን ብር ለመሰብሰብ ቢታቀድም ምንም ገቢ መሰብሰብ አለመቻሉንም አብራርተዋል፡፡

በኮምቦልቻ ገቢዎች ሚኒስቴር እና ጉምሩክ ኮምሽን ቅርንጫፎች 2.3 ቢሊየን ብር ለመሰብሰብ ታቅዶ የነበረ ቢሆንም በነበረው የሽብር ቡድኑ ወረራ ምክንያትም 1.9 ቢሊየን ብር ብቻ ለመሰብሰብ መቻሉን ተናግረዋል፡፡

ወ/ሮ ኡሚ አክለውም ጦርነቱ በአገር ኢኮኖሚ ላይ ያደረሰው ጫና በገቢው ዘርፍም የተስተዋለ ከመሆኑም በላይ ጦርነቱ በተካሄደባቸው አካባቢዎች ያሉ የኮምቦልቻ ገቢዎች ቅርንጫፍ ጽ/ቤት እና ጉምሩክ ቅርንጫፍ ጽ/ቤት ሙሉ በሙሉ በአሸባሪዎች የወደመ መሆኑንም አስረድተዋል፡፡

በቀጣይም ሰላም በተመለሰባቸው ቅርንጫፎች በፍጥነት ወደተግባር በመግባት በገቢው ዘርፍ የሚታየውን ክፍተት ለመሙላት ጥረት እንደሚደረግም የሚኒስቴሩ የኮሙዩኒኬሽን ዳይሬክተር ወ/ሮ ኡሚ አስታውቀዋል፡፡

መረጃው የገቢዎች ሚኒቴር ነው

ኢትዮ ኤፍ ኤም 107.8 የኢትዮጵያውያን
ታህሳስ 20 ቀን 2014 ዓ.ም

FacebooktwitterredditpinterestlinkedinmailFacebooktwitterredditpinterestlinkedinmail

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *