ሉአላዊነትን ማስጠበቅ የአዲሱ አመት ዋነኛ የዲፕሎማሲ ስራዎቻችን የትኩረት አቅጣጫ ይሆናል አለ የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር

ሚኒስትር መስሪያ ቤቱ የሃገርን አንድነት እና ሉአላዊነት ለማስጠበቅ በአለም አቀፍ ደረጃ ስኬታማ ያለውን የዲፕሎማሲ ስራዎችን መስራት መቻሉን የውጪ ጉዳይ ቃል አቀባይ አምባሳደር ዲና ሙፍቲህ ዛሬ ለጋዜጠኞች በሰጡት መግለጫ ገልጸዋል፡፡

የ100 ቀናት የመስሪያ ቤቱ የስራ አፈፃፀም ከፕላን እና ልማት ሚኒስቴር እንዲሁም የጠቅላይ ሚኒስትር ጽህፈት ቤት አመራሮች በተገኙበት መገምገሙንም አምባሳደሩ ጠቁመዋል፡፡

ኢትዮጵያ ከየትኛውም ሃገር ጋር ያላት ግንኙነትም ጥቅምን ያስጠበቀ እንደሆነ የገለጹት አምባሳደር ዲና ከአሜሪካን ጋርም ቢሆን ያለው ሁኔታም ይሻሻላል የሚል እምነት እንዳላቸው አስታውቀዋል፡፡

መስሪያ ቤታቸው የዲያስፖራን መምጣት እና የተሳካ ቆይታ እንዲኖራቸውም በርካታ የቅድመ ዝግጅት ስራዎችን እንዳጠናቀቀ ገልጸዋል፡፡

በተለያዩ መርሃ ግብሮች ዲያስፖራው ሃገርን እንዲጠቅም ለማድረግ የሚያስችሉ ስራዎችም መጠናቀቃቸውን አምባሳደር ዲና አመላክተዋል፡፡

የፐብሊክ ዲፕሎማሲ ስራዎችን በተመለከተም በሃገር ውስጥ አራት የከፍተኛ ትምህርት ተቋማትን ተሳታፊ ማድረግ መቻሉንን እና ተጨማሪ ሶስት ዩኒቨርስቲዎች ላይ ስራዎች እየተከናወኑ እንደሚገኙም የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር ቃል አቀባይ አምባሳደር ዲና ሙፍቲህ በሰጡት መግለጫ አስታውቀዋል፡፡

አብድልሰላም አንሳር
ታህሳስ 21 ቀን 2014 ዓ.ም

FacebooktwitterredditpinterestlinkedinmailFacebooktwitterredditpinterestlinkedinmail

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *