ቡና ባንክ በለውጥ ልህቀት ዘርፍ ዓለም አቀፍ ሽልማት አገኘ

ቡና ባንክ በለውጥ ልህቀት ዘርፍ በኮር ባንኪንግ ባስመዘገበው የላቀ አፈጻጸም የ7ኛው 2021 ዓለም አቀፍ ሽልማት አሸናፊ ሆኗል።

ባንኩ አሸናፊ የሆነው በውድድሩ ተሳታፊ ከነበሩ 270 የፋይናንስ ተቋማት ውስጥ በመካከለኛ ደረጃ ባንኮች መካከል በተካሄደ ውድድር ነው።

በዚህ ውድድር ቡና ባንክ በኮር ባንኪንግ የላቀ አፈጻጸም የሁለተኛ ደረጃ ሽልማት አሸናፊ ሆኗል።

ውድድሩ የተካሄደው በምርት ፈጠራ፣ በአቅርቦት ፈጠራ፣ በደንበኞች አገልግሎት ማሻሻያ፣ በኮርፖሬት ባንኪንግ፣ በዲጂታላይዜሽን፣ በአካባቢ ተኮር ፈጠራ፣ በስራ ሂደት ማሻሻያ፣ በለውጥ ልህቀት፣ በዘመናዊ ቴክኖሎጂ መር ፈጠራ፣ በቢዝነስ ሞፈዴል ፈጠራ፣ እና በኮቪድ ምላሽ ፈጠራ ዘርፎች ነው።

ከመላው ዓለም የተውጣጡ 270 ያህል የባንክና ፋይናንስ ተቋማት ተወዳዳሪዎች በነበሩበትና በ10 ዘርፎች ተከፍሎ በተካሄደው በዚሁ ውድድር ላይ ቡና ባንክ በለውጥ ልህቀት ምድብ የኮር ባንኪንግ ዘርፍ የላቀ አፈጻጸም ይዞ በመቅረብ ተወዳድሮ ነው አሸናፊ የሆነው።

ባንኩ ለዚህ ውጤት የበቃው በተጠቃለለው 2021 የፈረንጆች ዓመት ዘርፍ ባስመዘገበው ለውጥ እና በተለይም በኮር ባንኪንግ አፈጻጸም ባስመዘገበው የላቀ ውጤት ተመርጦ ነው።

ሔኖክ ወ/ገብርኤል
ታህሳስ 21 ቀን 2014 ዓ.ም

FacebooktwitterredditpinterestlinkedinmailFacebooktwitterredditpinterestlinkedinmail

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *