“በማህበራዊ መገናኛ ዘዴዎች የኢትዮጵያ ካርታ ተብሎ የሚሰራጨው ምስል ከእኔ ጋር ግንኙነት የለውም “ የአስተዳደር ወሰን እና ማንነት ጉዳዮች ኮሚሽን፡፡

ኮሚሽኑ ምስሉን እንደማያውቀው እና በመረጃው ላይ የተጠቀሰውም የአፍሪካ ህብረት የስራ ተቋም የሌለ መሆኑን ገልጿል፡፡

ኮሚሽኑ የአስተዳደር ጉዳዮችን በተመለከተ እያካሄደ ያለውን ሰፊ ጥናት ወደማገባደዱ እየተቃረበ እንደሚገኝ የገለፀ ሲሆን ነገር ግን ውጤቶችን ከመግለፅ ተቆጥቧል፡፡

ችግሮቹ ተለይተው እና ጥልቅ ምርምሮች ከተካሄዱ በኋላ ህዝባዊ ውይይቶችን እንደሚያደርግ ያስታወቀው ኮሚሽኑ በቀጣይም ምክረ ሃሳቦቹን ለሚመለከታቸው አካላት እንደሚያቀርብም አስታውቋል፡፡

ኮሚሽኑ ሃገራችን ካጋጠማት ጦርነት ጋር በተያያዘም ስራዎቹ ላይ እንቅፋት እንደገጠማቸው አስታውቋል፡፡

ከእንቅፋቶቹም መካከል ውስን ዞኖች እና ልዩ ወረዳዎች አለመተባበራቸው የፀጥታ ስጋት መኖሩ እና የኮሮና ቫይረስ ወረርሽኝም ዋና ዋናዎቹ መሰናክሎች እንደነበሩ አስታውቀዋል፡፡

ኮሚሽኑ ከተሰጠው ጊዜ አንፃር አስፈላጊውን ሁሉ በማድረግ የተሻለን ጥናት እና ምክረ ሃሳብ ለማቅረብ እየጣረ እንደሚገኝ የገለፀ ሲሆን ነገር ግን በይድረስ ይድረስ ጥናቱን እንደማያጠናቅቅ አስታውቋል፡፡

በመሆኑም ጉዳዩን ለምክርቤቱ በማቅረብ በአዋጁ መሰረት ኮሚሽኑ ተጨማሪ ጊዜ እንዲሰጠው እንደሚጠይቅም የኮሚሽኑ ዋና ሰብሳቢው ዶ/ር ጣሰው ገብሬ ተናግረዋል፡፡

የአስተዳደር ወሰን እና ማንነት ጉዳዮች ኮሚሽን በአዋጅ የተሰጠው የጊዜ ገደብ ሶስት አመታት ብቻ እንደነበርም አይዘነጋም፡፡

አብድልሰላም አንሳር
ታህሳስ 22 ቀን 2014 ዓ.ም

FacebooktwitterredditpinterestlinkedinmailFacebooktwitterredditpinterestlinkedinmail

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *