የሱዳን ወታደራዊ ሃይል በካርቱም የሚገኙ የአልአረቢያ እና የአልሃደስ ቴሌቪዥን ጣቢያዎችን መክበቡን እና ንብረታቸውንም መውረሱ ተዘግቧል፡፡

ወታደራዊው ሃይል ይህንን ሲያደርግም የሚያሳይ የሲሲቲቪ ተንቀሳቃሽ ምስልም በጣቢያዎቹ የሚገኙ ሰራተኞችን ሲያንገላቱ እና ጥቃት ሲሰነዝሩባቸው ያሳያል፡፡

በዱባይ መቀመጫውን ያደረገው አልአረቢያ ቴሌቪዥን በርካታ ጋዜጠኞቹ እና ሰራተኞቹ መጎዳታቸውን አስታውቋል፡፡

በካርቱም የህዝቡ አመፅ እና ተቃውሞው እንደቀጠለ ሲሆን ወታደራዊ ሃይሉ ተጨማሪ አራት ሰዎችን ሳይገድል እንዳልቀረም ተዘግቧ፡፡

በተለይም በኡምዱርማ እና በካርቱም ሰሜናዊ አካባቢዎች ተቃውሞውም የወታደሩም እርምጃ የከረረ እንደነበር በዘገባው ታትቷል፡፡

የተባበሩት መንግስታት እና በካርቱም የሚገኘው የአሜሪካ ኤምባሲ የሰልፈኞቹን መገደል በብርቱ አውግዘዋል፡፡

ምንጭ፡- Africa News

አብድልሰላም አንሳር
ታህሳስ 22 ቀን 2014 ዓ.ም

FacebooktwitterredditpinterestlinkedinmailFacebooktwitterredditpinterestlinkedinmail

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *