የቀድሞ የኢትዮጵያ ሰራዊት ባንክ ሊመሰርት ነው፡፡

ከተመሰረተ ከሶስት አመታት በላይ ያስቆጠረው የቀድሞ የኢትዮጵያ ሰራዊት የልማት እና የመረዳጃ ማህበር፣ የማህበሩን ኢኮኖሚ ለማጠናከር የአባላቱን ተጠቃሚነት ለማሳደግ በማሰብ ባንክ ሊመሰርት እንደሆነ ሰምተናል፡፡

የቀድሞ የኢትዮጵያ ሰራዊት የልማት እና የመረዳጃ ማህበር ፕሬዝዳንት 50 አለቃ ብርሀኑ አማረ ለኢትዮ ኤፍ ኤም እንደተናገሩት ላለፉት 27 አመታት፣ የኢትዮጵያ ባለውለታ የነበረው የቀድሞ ሰራዊት እራሱን በኢኮኖሚ እንዳያሳድግ ከፍተኛ ጫና ሲደረግበት እንደነበር አንስተው ይሄን ሁኔታ ለመቀየር የሚቻልበት ምቹ ሁኔታ በመኖሩ ሃሳቡ መነሳቱን ነግረውናል፡፡

ከአንድ ሚሊየን በላይ አባላት ያለው የቀድሞ የኢትዮጵያ ሰራዊት የልማት ማህበር የሚመሰርተረው ባንክ “ አድማስ የማይክሮ ፋይናንስ” የሚሰኝ መሆኑን ነው ፕሬዝዳንቱ የተናገሩት፡፡

መላው ኢትዮጵያዊያን የሰራዊቱን ኢኮኖሚ ለማሳደግ በሚደረገው ጥረት ሁሉ የበኩላቸውን ሊወጡ እንደሚገባ ያለሱት የማህበሩ ፕሬዝዳንት ፣ የባንኩ ምስረታ የፊታችን እሁድ የመንግስት እና የማህበሩ አባላት በተገኙበት ይፋ ይደረጋል ብለዋል፡፡

የቀድሞ የኢትዮጵያ ሰራዊት የልማት እና መረዳጃ ማህበር በዶሮ እርባታ፣ በሆቴል ሙያ ስልጠና በጥበቃ አገልግሎት በግብርና እና በሌሎችም ማህበሩን በሚያጠናክሩ ስራዎች ላይ እየተሳተፈ ይገኛል፡፡

በአዲስ አበባ እና በክልል ከተሞች 279 ቅርንጫፎችን ከፍቶ የልማት ስራዎች እየሰራ የሚገኝው ማህበሩ ፣የባንኩ መመስረት አባላቱን የበለጠ ተጠቃሚ ለማድረግ እንደሚረዳ አንስተዋል፡፡

የአድማስ የማይክሮ ፋይናንስ አባል ለመሆን እና ሌሎች ጉዳዮችን በተመለከተ የፊታችን እሁድ በሚኖረው መርሃ ግብር ይፋ እንደሚሆን ፕሬዝዳንቱ ከጣቢያችን ጋር በነበራቸው የስልክ ቆይታ ነግ ረውናል፡፡

ሔኖክ ወ/ገብርኤል
ታህሳስ 22 ቀን 2014 ዓ.ም

FacebooktwitterredditpinterestlinkedinmailFacebooktwitterredditpinterestlinkedinmail

Leave a Reply

Your email address will not be published.