በመዲናዋ በደረሱ ሁለት ድንገተኛ አደጋዎች በሶስት ሰዎች ላይ ከባድ ጉዳት ደረሰ፡፡

በአዲስ አበባ በሁለት ክፍለ ከተሞች በደረሱ ድንገተኛ አደጋዎች በሰው እና በንብረት ላይ ጉዳት መድረሱን የእሳት እና የአደጋ ስጋት ስራ አመራር ኮሚሽን አስታወቀ፡፡

የኮሚሽኑ የህዝብ ግኑኝነት ሃላፊ አቶ ጉልላት ጌታነህ ለኢትዮ ኤፍ ኤም እንደተናገሩት በከተማዋ በሁለት ቀናት ወስጥ በደረሱ አደጋዎች ምክንያት ከአንድ ሚሊየን ብር በላይ የሚጠጋ ንብርት ለጉዳት ተዳርጓል ብለዋል፡፡

የመጀመርያው የእሳት አደጋ የደረሰው በኮልፌ ቀራኒዮ ክፍለ ከተማ ወረዳ 2 መድሀኒያለም ቤተ ክርስቲያን አካባቢ በሚገኝ እንጨት ቤት ላይ ነው፡፡

በዚህ አደጋ ምክንያት 100ሺህ ብር የሚጠጋ ንብረት ለውድመት የተዳረገ ሲሆን 4 ሚሊየን ብር የሚጠጋ ንብረት ደግሞ ማዳን መቻሉ ተገልጻል፡፡

ሁለተኛ ድንገተኛ አደጋ የደረሰው በየካ ክፍለ ከተማ ወረዳ 9 ላምበረት ተብሎ በሚጠራው አካባቢ ሲሆን ሁለት ተሽከርካሪዎች ተጋጭተው ያደረሱት አደጋ ነው፡፡

በአደጋው አንድ ወንድ እና ሁለት ሴቶች ከፍተኛ የአካል ጉዳት ደርሶባቸዋል፡፡

ከዚሁ አደጋ ጋር በተያያዘም ወደ 7 ሚሊየን ብር የሚጠጋ ንብረት ሙሉ በሙሉ ከጥቅም ውጭ መሆኑንም ነው አቶ ጉልላት ለጣቢያችን ተናግረዋል፡፡

ሔኖክ ወ/ገብርኤል
ታህሳስ 25 ቀን 2014 ዓ.ም

FacebooktwitterredditpinterestlinkedinmailFacebooktwitterredditpinterestlinkedinmail

Leave a Reply

Your email address will not be published.